
የስሚዞንያን ናሽናል ዙ ማክሰኞ ኦክቶበር 15 ሁለት ፓንዳዎችን ከቻይና ተረክቦ እንደነበር ይታወቃል። ከአመት በፊት 2 ፓንዳዎች የውሰት ዘመናቸው በማለቁ ወደ ቻይና ተመልሰው ነበር:: ከ11 ወራት በሁዋላም ባሳለፍነው ኦክቶበር ባኦ ሊ እና ቺንግ ባኦ የተባሉ ፓንዳዎች ወደ መካነ አራዊቱ ተቀላቅለው ነበር።
ላለፉት ሳምንታት ታዲያ የመካነ አራዊቱ ባለሞያዎች እኚህን ፓንዳዎች ለዲሲ አየር ሲያለማምዷቸው የቆዩ ሲሆን በተያዘላቸው ቀጠሮ መሰረትም ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ፓዳዎቹ ለህዝብ ምልከታ ክፍት ይሆናሉ። ምንም እንኳ ወደ ናሽናል ዙ ለመግባት ክፍያ ባያስፈልገውም ጎብኚዎች ነጻ የመግቢያ ትኬት ከመሄዳቸው በፊት መቁረጥ እንዳለባቸው ተጠቁሟል። ቲኬቱን ለመቁረጥ ይህን ይጫኑ።
የፓንዳዎቹን ለህዝብ ክፍት መሆን አስመልክቶም የዲሲ ሜትዎ የመታሰቢያ የሜትሮ ካርድ አሳትሟል።
በቦታው በአካል መገኘት የማይችሉ ደሞ ኦንላየን በቀጥታ የሚሰራጩ ቪዲዮችን ማየት እንደሚችሉ የመካነ አራዊቱ አስተዳዳሪዎች አስታውቀዋል።
ይህን ተጭነው ፓንዳዎቹን በቀጥታ ይመልከቱ