ተገኝታለች (5)

የትራምፕ ዋይት ኃውስ ትላንት እሁድ በኤክስ ገጹ ላይ ባወጣውና በአይስ በቁጥጥር ስር አውዬ ወደአገራቸው ዲፖርት አረጋቸዋለሁ ካላቸው ስደተኞች መኃከል አንዱ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ አስታውቀዋል። ይህ ግለሰብ ያሬድ ገረመው መኮንን የሚባል ሲሆን በወሲባዊ ጥቃት ወንጀለኛ ተብሎ የተፈረደበት ግለሰብ እንደሆነ አክለው አስታውቀዋል።

በወቅቱ የ24 አመት ወጣት የነበረው ያሬድ መኮንን በሜይ 28 2017 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ በታክሲ አሽከርካሪነት ሲሰራ አንድ ምሽት በመጠጥ የሰከረች ሴት እንዳሳፈረና ሴትየዋ ራሷን ስታ እንደነበር። ስትነቃ ያሬድ ያለፍቃዷ በግብረስጋ እየተገናኛት እንደነበረ የፖሊስ ሪፖርት ላይ ተመዝግቧል። ይህን ጊዜ ተሳፋሪዋ ደንግጣ መጮህ ስትጀምር ያሬድ መኪናውን አስነስቶ መሄድ ይጀምራል። እንዲለቃት ብትለምነውም ሊለቃት ፈቃደኛ አልነበረም። ይህን ጊዜ ተሳፋሪዋ የመኪናውን መሪ በመያዝ መጮህ ጀመረች። ጩኸቷን የሰሙ የአካባቢው ሰዎች ታዲያ በ4900 block of 16th Street NW አቅራቢያ ታክሲውን አስቆሙት። ፖሊስ ሲመጣ ያሬድ የተባለውን አላረኩም ሲል ክዷል።

ያሬድ በ16 ስትሪት ሄይትስ አካባቢ በዲሲ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ታይቶ የነበረ ሲሆን። በወቅቱም ክሱ በፍርድ ቤት ሲታይ እንደነበር ዘገባዎች ጠቁመዋል።

ያሬድ ታዲያ ባሳለፍነው ሰሞን ጃንዋሪ 24 2025 በኒው ኦርሊንስ በአይስ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ዋይትኃውስ አስታውቋል።

የትራምፕ አስተዳደር ስልጣኑን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ ያለማሰለስ ህገዋጥ ናቸው ያላቸውን ስደተኞች በማፈስ ላይ እንደሆነ አስታውቋል። በትላንትናው እለት ብቻ 956 ህገዋጥ ናቸው ያላቸውን ስደተኞች ማሰሩን አይስ አስታውቋል።

Source: https://x.com/ICEgov

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.