@ethiopique202 (3)

ፕሬዘደንት ትራምፕ ከሰሞኑ በዳውን ታውን ሲልቨርስፕሪንግ በሚገኘው የNOAA መስሪያ ቤት ይሰሩ የነበሩ ከ1000 በላይ የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ሰራተኞችን ከስራ አባረዋል። የመንግስት ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የአየር ሁኔታ ትንበያ እንደ አንድ የመንግስት አገልግሎት ሆኖ ለህብረተሰቡ በነጻ ሲሰጥ ቆይቷል።
ይህ የነጻ አገልግሎት ታዲያ የአሜሪካ ገበሬዎች፤ አሳ አጥማጆች እንዲሁም ተራው ህዝብ በሙሉ ለዕለት ተዕለት ጉዳዩ ይገለገልበታል። በየጊዜው በሚወጡት የቶርኔዶ፤ የሁሪኬን፤ የከባድ ዝናብ፤ የሀይለኛ በረዶ ትንበያዎች በየጊዜው በርካቶችን ከሞት ወይንም ከንብረት ጥፋት ታድጓል። የአሜሪካ አየር ንብረት አገልግሎት ከ1870 ጀምሮ በኮንግረስ የተቋቋመ መንግስታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ነው። የአሁን መጠሪያ ስሙ የናሽናል ዌዘር ሰርቪስ ሲሆን በናሽናል ኦሺያኒክ ኤንድ አትሞስፌሪክ አድሚንስትሬሽን ስር ሆኖ ይተዳደራል። የሰበሰበውን የአየር ሁኔታ መረጃ በመተርጎምም ለህዝቡ ያደርሳል። ዋነኛ አላማውም የሰውን ህይወትና ንብረት ከተፈጥሯዊ ጥፋቶች መታደግ ነው።

ከጊዜ ወዲያ የተቋቋሙት እንደ አኩዌዘር የመሳሰሉ አትራፊ ድርጅቶች ይህን የመንግስት አገልግሎት ለማዘጋትና ህብረተሰቡ የአየር ሁኔታ ትንበያን በክፍያ ማግኘት እንደሚገባው ሲወተውቱ እንዲሁም ሎቢ ሲያደርጉ ቆይተዋል። የአየር ንብረት ትንበያ የበርካታ ቢልየኖች ፈሰስ ያለበት ኢንደስትሪ ነው። ከትናንሽ ጀማሪ ድርጅቶች እስከ ትልልቆቹ ጉግልና ማይክሮሶፍት ይህንን አገልግሎት ለደንበኞቻቸው ያቀርባሉ።

የአኩ ዌዘር መስራችና ሲ ኢ ኦ በ2018 ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ዩኒየን ፓሲፊክ የተባለ የአኩዌዘርን የአየር ትንበያ አገልግሎት የሚጠቀም የባቡር ድርጅት በመስመሮቹ ላይ ያለ ቶርኔዶ ስለተነገረው በዛ መስመር የሚያልፉ ሁለት ባቡሮችን እንዲይቆሙ እንደነገሯቸውና በሁለቱ ባቡሮች መሀከል ቶርኔዶ እንዳለፈ በዚህም ባቡሮቹ ከአደጋው ማምለጥ እንደቻሉ ሆኖም ቶርኔዶው ከዛ አለፎ ወዳለች አነስተኛ ከተማ እንደሄደና በዛ ግን የአኩዌዘርን አገልግሎት የሚጠቀም ተቋምም ሆነ ግለሰብ ባለመኖሩ ሁለት ደርዘን ያህል ሰው በአደጋው ለህልፈት እንደተዳረገ ተናግረዋል።

በፕሬዘደንት ትራምፕ ተቃዋሚዎች ዘንድ ትልቅ አጀንዳ በነበረው የፕሮጀክት 2025 የወግ አጥባቂዎች (ኮንሰርቫቲቭ) መመሪያ ዶሴ ላይም የብሄራዊ ሜትሮሎጂ አገልግሎትና እናት ድርጅቱ ናሽናል ኦሼያኒክ ኤንድ አትሞስፌሪክ አድሚንስትሬሽን እንዲዘጋና ትኩረቱን አገልግሎቱን ለህዝብ በነጻ ከማቅረብ ይልቅ የአየር ሁኔታን ዳታ መሰብሰብ ላይ ብቻ እንዲያተኩርና እንደአኩዌዘር ላሉ የግል ተቋማት ይህን ዳታ በመሸጥ እንዲተዳደር በዚህም ራሱን በገንዘብ እንዲችል መክረዋል።

የቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች ይህን ተቋም በዋናነት የአለም ሙቀት መጨመርንና የአየር ንብረት ለውጥን (Climate Change)ን በማጋነን ያቀርባል ሲኡ ይከሱት ነበር። ይህንንም ተከትሎ የተሰበሰበውን መረጃ የመተርጎም ስራ ለግል ድርጅቶች እንዲተውና መንግስት ራሱን ከዚህ አገልግሎት እንዲያገልም ሲመክሩ ይስተዋላል።

እርስዎ እስካሁን በስልክዎ በነጻ ያገኙት የነበረውን የአየር ትንበያ ለማግኘት ምን ያህል ቢከፈለው ጥሩ ነው ይላሉ?

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.