
የፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ ጤና ቢሮ ትላንት ፌብሯሪ 28 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በካውንቲው በተለይም በ5700 ሊቪንግስተን ሮድ ኦክሰን ሂል አካባቢ ፌብሩሪ 24 ምሽት 6pm ገደማ በጣም የታመመና የደከመ አጋዘን እንደታየና በአካባቢው የነብሩ ሰዎች ባደረጉት ጥቆማ የተፈጥሮ ጥበቃ መስሪያቤት አባላት በቦታው በመገኘት አጋዘኑን እንደገደሉትና ለምርመራ ወደ ሜሪላንድ ጤና ቢሮ እንደተላከ የምርመራ ውጤቱ ትላንት ፌብሯሪ 28 ሲመጣም የእብድ ውሻ በሽታ (ሬቢስ) እንደነበረበት እንደተረጋገጠ አስታውቀዋል።
ይህን ተከትሎም የካውንቲው ጤና ቢሮ ከፌብሯሪ 14 እስከ 24 ባለው ጊዜ ውስጥ በተጠቀሰው አካባቢ ከአጋዘንጋ ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ወይንም እንስሳት ካሉ ወደ ካውንቲው ጤና ቢሮ ሄደው ወይንም በስልክ ቁጥር 301-583-3751 ወይንም 240-508-5774 ደውለው እንዲጠቁሙ ተጠይቋል።
ሙሉ የካውንቲውን መግለጫ ለማየት ይህን ይጫኑ።