
የቴክሳስ ፖሊስ እንዳሳወቀው ትላንት አርብ በ3100 N IH 35 SB (between Parmer Ln & Howard Ln). በተከሰተ የመኪና አደጋ 17 መኪኖች ሲጋጩ አድ ታዳጊና አንድ አራስን ጨምሮ በጠቅላላው 5 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።
ፖሊስ አደጋውን አድርሷል ያለውን ተጠርጣሪም ይፋ አድርጓል።
በፖሊስ ሪፖርት መሰረትም የአደጋው አድራሽ የ37 አመት እድሜ ያለው ሰለሞን አርአያ እንደሆነና ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ለፍርድ እንደሚያቀርበው ታውቋል።
እንደፖሊስ ገለጻ ከሆነ ሰለሞን በ5 ሰክሮ በማሽከርከር የነፍስ ማጥፋት ወንጀሎችና በ2 ሰክሮ በመተንኮስ ወንጀሎች ክስ እንደሚያቀርብበት አስታውቋል።
ፖሊስ በአደጋው ወቅት በርካታ ሰዎች በመኪናቸው ውስጥ ተጣብቀው እንደተገኙና ከሟቾች በተጨማሪ 12 ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ አስታውቋል። ከተጎዱት 12 ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ ህጻናትና ታዳጊዎች እንደሆኑም ፖሊስ አክሎ ገልጿል።
ሰለሞን በወቅቱ ባለ18 ጎማ ተሳቢ (18 ዊለር ሴማይ ትራክ) ያሽከረክር እንደነበር ተገልጿል።
ለዜናው ሀቢብ ጀማልን እናመሰግናለን።