Customize Consent Preferences

We use cookies to help you navigate efficiently and perform certain functions. You will find detailed information about all cookies under each consent category below.

The cookies that are categorized as "Necessary" are stored on your browser as they are essential for enabling the basic functionalities of the site. ... 

Always Active

Necessary cookies are required to enable the basic features of this site, such as providing secure log-in or adjusting your consent preferences. These cookies do not store any personally identifiable data.

No cookies to display.

Functional cookies help perform certain functionalities like sharing the content of the website on social media platforms, collecting feedback, and other third-party features.

No cookies to display.

Analytical cookies are used to understand how visitors interact with the website. These cookies help provide information on metrics such as the number of visitors, bounce rate, traffic source, etc.

No cookies to display.

Performance cookies are used to understand and analyze the key performance indexes of the website which helps in delivering a better user experience for the visitors.

No cookies to display.

Advertisement cookies are used to provide visitors with customized advertisements based on the pages you visited previously and to analyze the effectiveness of the ad campaigns.

No cookies to display.

@ethiopique202 (10)

የዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ አካባቢ በርካታ ለአሳ ማጥመጃ የሚሆኑ ቦታዎች አሏቸው። ከረጅሙ የፖቶማክ ወንዝ አንስቶ እስከ ሰፊው የቸሰፒክ ቤይ እንዲሁም በየቦታው ያሉት ሀይቆች ለአሳ ማጥመጃ ምቹ ፓርኮች አሏቸው።

እነዚህን ቦታዎች በከፊል ዳሠናቸዋል እነሆ። በመጀመሪያ ጨዋማ ያልሆኑ የውሀ አካላትን

ፖቶማክ ወንዝ (ዲሲ ሜሪላንድ ቨርጂንያ)


በፖቶማክ ወንዝ ላይ አሳ ለማጥመድ የኢትዮጲክ ባልደረቦች ምርጫ የሆኑት ሁለት ቦታዎች ናቸው።

አንደኛው በጆርጅታውን አቅራቢያ በ4940 Canal Rd NW, Washington, DC 20016 የሚገኘው ፍሌቸርስ ኮቭ ተብሎ የሚጠራው ስፍራ አሳ ለማጥመድም ጀልባ/ታንኳ ተከራይቶ ለመዝናናትም የሚሆን አነስተኛ ስፍራ ነው።

ካት ፊሽ – ኢስት ፖቶማክ ፓርክ- ዲሲ

ሌላኛው ደሞ የኢስት ፖቶማክ ፓርክ የሚገኘው የሄነስ ፖይንት ቼሪ ብሎሰም አካባቢ ነው። በ927 Ohio Dr SW, Washington, DC 20024 አቅራቢያ የሚገኘው ይህ ስፍራ ከፖቶማክ ወንዝ በተጨማሪ በጀርባው ያለውን የዋሽንግተን ቻናልን ለአሳ ማጥመጃ ለመጠቀም ያስችላል።
በዚህ አካባቢ እንደ ወቅቱ የተለያዩ የአሳ ዝርያዎች የሚገኙ ሲሆን በዋናነት ላርጅ ማውዝ ባዝ፤ ስሞል ማውዝ ባዝ፤ ሄሪንግ፤ ዋይት ፐርች፤ ብሉ ካትፊሽ(አምባዛ)፤ ቻነል ካትፊሽ፤ ሰንፊሽና ስትራይፕድ ባዝ ይገኙበታል።

አናኮስትያ (ዲሲ)
ባሳውዝ ኢስት ዲሲ የሚገኘው አናኮስትያ ፓርክ ለበርካታ አመታት የዲሲ ቆሻሻ ይገባበታል በተለይም ሀይለኛ ዝናብ ከዘነበ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያው ወደ ወንዙ ስለሚገባ ብዙዎች አይደፍሩትም። ሆኖም በውስጡ በርካታ የአሳ ዝርያዎችን ይዟል። አናኮስትያ ላይ አሳ ለማጥመድ ምቹ ቦታዎች አንዱ በ1900 Anacostia Dr, Washington, DC 20020 የሚገኘው የአናኮስትያ ፓርክ ሲሆን ሌላው ደሞ በ575 Oklahoma Ave NE, Washington, DC 20019 የሚገኘው የኪንግማን ሄሪቴጅ ደሴት ፓርክ ናቸው።
ልክ እንደፖቶማክ ሁሉ ይህም ወንዝ በርካታ ካት ፊሽ (አምባዛ) ይገኝበታል። በተጨማሪም ላርጅ ማውዝ ባዝ፤ ዋይት ፐርችና ብሉጊል የተባሉ የአሳ ዝርያዎች ይገኙበታል።

ካትፊሽ (አምባዛ)- ሄይነስ ፖይንት-ዲሲ


ሌክ አና (ቨርጂንያ)
በተለይም በ3603 Moody Town Rd, Bumpass, VA 23024 በሚገኘው የሀይቁ የህዝብ አሳ ማጥመጃ ቦታ ለአሳ ማጥመድ አይነተኛ ቦታ ነው። በዚህ ቦታ ላይም የላርጅ ማውዝ ባዝ፤ ክራፒ፤ ብሉ ካትፊሽና ዎልአይ የተባሉ የአሳ ዝርያዎች ይገኛሉ።

ስትራይፕድ ባዝ – ሄነስ ፖይንት – ዲሲ

ብላክ ሂል ሪጅናል ፓርክ (ሊትል ሴኔካ ሌክ) ሜሪላንድ
በሜሪላንድ በ20930 Lake Ridge Dr, Boyds, MD 20841 የሚገኘው ይህ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ከአሳ ማጥመጃ በተጨማሪ የተዋበና ሰላማዊ ፓርክ እንዲሁም የጀልባ ኪራይ አገልግሎት በተወሰኑ ሰዓታት ይሰጣሉ። በዚህ ቦታ እንደ ላርጅ ማውዝ ባዝ፤ ስኔክ ሄድ፤ የሎው ፐርችና ብሉ ጊል የመሳሰሉ የአሳ ዝርያዎች ይገኛሉ።


ዊተን ሪጅናል ፓርክ ኩሬ
በሲልቨር ስፕሪንግ አቅራቢያ የሚኖሩ ከሆነና ከስራ መልስ ቤት ከመግባትዎ በፊት ለ30-40 ደቂቃ የምትሆን ጊዜ አሳ ለማጥመድ ከፈለጉ የዊተን ሪጅናል ፓርክ የሚገኘው ፓይን ሌክ ወሳኝ ቦታ ነው። በዚህ ሀይቅ ብሉ ጊልና ላርጅ ማውዝ ባዝ በብዛት ይገኛሉ።

ላርጅ ማውዝ ባዝ – ዊተን ፓርክ ኩሬ (Pine Lake)

ጨዋማ ወሀዎች

ቸሰፒክ ቤይ (ሜሪላንድና ቨርጂንያ)
ከባልቲሞር በስተሰሜን ከሚገኘው ከሳስኩዋሃና ሜሪላንድ ጀምሮ እስከ አትላንቲክ ውቅያኖስ በተዘረጋው በቸሰፒክ ቤይ ላይ ባሉ በርካታ ፓርኮችና የህዝብ አሳ ማጥመጃዎች ለአካባቢው ህዝብ አገልግሎት ይሰጣሉ። በቸሰፒክ ቤይ ላይ አሳ ለማጥመድ የኢትዮጲክ ምርጫ የሆኑት ቦታዎች ፎርት ስሞልውድ ፓርክ፤ ዳውንስ ፓርክ፤ ቶማስ ፖይንት ፓርክ፤ ማታፒክ ፓርክ፤ ሮማንኮክ ፓርክ፤ ፖይንት ሉካውት ፓርክና ሰለሞን አይላንድ ይገኙበታል። ወደፊት የሁሉንም ፓርኮች አንድ በአንድ እንመለስባቸዋለን።

ማንታ ሬይ (ስቲንግ ሬይ) – ዳውንስ ፓርክ


በቸሰፒክ ቤይ እንደትልቅ ስኬት የሚቆጠረው የስትራይፕድ ባዝ አሳን ማጥመድ ነው።በተጨማሪም ግን እንደ ብሉ ክራብ፤ ስፔክልድ ትራውት፤ ክሮከር፤ ፍላውንደር፤ ብሉ ፊሽ፤ ዋይት ፐርች፤ ሬድ ድራም እና ማንታ ሬይ (ስቲንግ ሬይ) የመሳሰሉ የአሳ ዝርያዎች አሉ።


ቨርጂንያ ቢች (ቨርጂንያ)
ቨርጂንያ ቢች በርካታ የአሳ ማጥመድ አይነት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ስላሉ ከሌሎቹ የበለጠ መዝናናትና አድቬንቸር ያላቸው እንደ ዲፕ ሲ ቻርተርና ሰርፍ ፊሺንግ የመሳሰሉ የአሳ ማጥመድ ፕሮግራሞች ላይ መሳተፍ ይቻላል። በአብዛኛው የሬድ ድራም፤ ኮቢያ፤ ኪንግ ማከሬል፤ ስፓኒሽ ማከሬልና ብላክ ሲባስ የተብሉ የአሳ ዝርያዎች ይገኛሉ።


ኦሽን ሲቲ ሜሪላንድ
ኦሽን ሲቲ ሜሪላንድም ልክ እንደ ቨርጂንያ ቢች የፒየርና ሌሎች የአሳ ማጥመድ አድቬንቸሮች ያሉት ሲሆን በዚህ አካባቢ የሚገኙ የአሳ ዝርያዎች ስትራይፕድ ባዝ፤ ብሉ ፊሽ፤ ፍላውንደር፤ ቱና እና የተለያዩ ዘር ያላቸው ሻርኮች ይገኙበታል።

ሻርክ – ኦሽን ሲቲ ሜሪላንድ

በዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ አሳ ለማጥመድ ማንኛውም እድሜው ከ16 ዓመት በላይ የሆነ ሰው የየስቴቱ እንዲሁም የየውኃ አይነቱ የማጥመጃ ፍቃድ ያስፈልጋል።


ዋሽንግተን ዲሲ – ለዲሲ ነዋሪዎች 10$ ከዲሲ ውጭ ለሚኖሩ ደሞ 13$ በአመት ያስከፍላል። ፍቃድ ለማውጣት በኦንላይን ይህን ሊንክ በመጫን ማውጣት ይችላሉ።


ሜሪላንድ – የሜሪላንድ ነዋሪዎች እንደ ፍቃዱ አይነት በአመት ከ20.50$ ጀምሮ የሚከፍሉ ሲሆን የሜሪላንድ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ደሞ እንደ ውኃው አይነትና እንደፍቃዱ ጊዜ (ለጎብኚዎች የ3 ቀን ፍቃድ አለ) ከ$5 ጀምሮ በመክፈል የአሳ ማጥመጃ ፍቃድ ማውጣት ይችላሉ። ፍቃድ ለማውጣት በኦንላይን ይህን ሊንክ በመጫን ማውጣት ይችላሉ።


ቨርጂንያ – ልክ እንደሜሪላንድ የተለያየ የአሳ ማጥመጃ የክፍያ መደብ አላቸው። ፍቃድ ለማውጣትና የዋጋ ዝርዝሩን ለማየት በኦንላይን ይህን ሊንክ በመጫን ማውጣት ይችላሉ።

ከአሳ ማጥመጃ ፍቃድ ውጪ በየወቅቱ የሚቀያየሩ ህጎችን ማወቅም ግዴታ ነው። ለምሳሌ በሜሪላንድ እንደ ትልቅ ስኬት የሚታየውን የስትራይፕድ ባስ (ሮክ ፊሽ) አሳ ከኤፕሪል 1 እስከ ሜይ 15 እንዲሁም ከጁላይ 16 እስከ ጁላይ 31 መያዝ ክልክል ነው። በተጨማሪም በተፈቀዱ ጊዜያት ደሞ ቁመታቸው ከ 19 ኢንች እስከ 24 ኢንች የሆኑ አሳዎችን ብቻ ነው መውሰድ የሚቻለው። በተጨማሪም በሜሪላንድ በአንድ ጊዜ አንድ ሰው ከአንድ የስትራይፕድ ባስ አሳ በላይ መውሰድ አይፈቀደም። እነዚህንና ሌሎች በርካታ ደንቦች ጥሶ የተገኘ ሰው በየስቴቱ ቅጣት ይጠብቀዋል። ቅጣቱም ከገንዘብ እስከ እስር ሊደርስ ይችላል። ስለ ህግና ደንቦቹ በደንብ እውቀት ለሌለው ሰው የያዙትን አሳ መልሰው ወደ ውሀ እንዲጥሉ ይመከራሉ። የሜሪላንድቨርጂንያና ዲሲን ህግጋት ለማወቅ ስማቸውን ይጫኑ።

አየሩ ሞቅ እያለ ሲመጣ የኢትዮጲክ ባልደረቦችና ወዳጆቻቸው ከቤት ውጪ እየተገናኘን ልጆቻችንን ይዘን የምንዝናናበትና የምንወያይበት እንዲሁም መሰረታዊ የህይወት ክህሎቶችን ለልጆቻችን የምናሳይበት የአሳ ማጥመድ ፕሮግራም ይኖረናል። ይህ ፕሮግራም በነጻ ማንኛውም ሰው መሳተፍ የሚችልበት ፕሮግራም ነው።

በዚህ በወር አንዴ ክረምት እስኪገባ ድረስ ለሚኖረው የአሳ ማጥመድ የቤተሰብ ፕሮግራም ለመሳተፍ ፍላጎት ካለዎት ይህን ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ። ፕሮግራሙ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.