
የአርሊንግተን ካውንቲ መንግስት በካውንቲው ውስጥ ቤት/ታውን ሀውስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት ለሚገዙ ሰዎች የገቢ መስፈርቱን ካሟሉ እስከ 25 ከመቶ የሚሆነውን የቤቱን ክፍያ እንዲሸፍኑ ከወለድ ነጻ የሆነ ብድር አዘጋጅቼያለሁ ብሏል፡፡
ይህ ገንዘብ ቤት ገዢዎች የቤት መግዣውን ቀብድ ክፍያ ወይንም ሌሎች ተያያዥ የመዝጊያ ወጪዎች (Closing Costs) እንዲሸፍኑ ያግዛል ተብሏል፡፡
ይህ ብድር እንደሁለተኛ ሞርጌጅ እንደሚቆጠርና በቀጥታ የሚከፈል ሳይሆን በተያያዥ ከመጀመሪያው ሞርጌጅጋ የሚከፈል እንደሆነና የቤቱ ባለቤቶች የገዙትን ቤት ለመሸጥ ከወሰኑ ወይንም ሪፋይናንስ ለማድረግ ከወሰኑና የቤቱ ዋጋ ከጨመረ በሂሳብ ተሰልቶ የተበደሩት ብድር የጨመረውን ያህል እንደሚጨምር ተገልጿል፡፡
በዚህ ከወለድ ነጻ ብድር ተጠቃሚ ለመሆን ታዲያ ተበዳሪዎች ከስር በሰንጠረዝዥ የተቀመጠውን የቤተሰብ ገቢ መስፈርት ማሟላት አለባቸው፡፡

ከገቢ በተጨማሪም የሚከተሉት ሁኔታዎች ብድሩን ለማግኘት እንደ መስፈርት ተቀምጠዋል፡፡
- የሚገዛው ቤት በአርሊንግተን ካውንቲ ውስጥ መሆን አለበት፡፡
- በዚህ መልካም እድል ለመጠቀም የሚገዙት ቤቶች እንደ ታውንሀውስ ዱፕሌክስና ራሱን የቻለ ቤት አልያም እንደ ኮንዶሚኒየም ያለ በርካታ ሰዎች የሚኖሩበት ቤት መሆን አለበት፡፡
- የቤቱ ከፍተኛ የመግዣ ዋጋ ከ500ሺ ዶላር መብለጥ የለበትም፡፡
- ከፍተኛው የብድር መጠን ከ25% ያልበለጠ ወይንም ከ112 ሺ 500 ዶላር ያልበለጠ፡፡
- ዝቅተኛው ቀብድ (ዳውን ፔይመንት) ፟ የጠቅላላ የቤቱ ዋጋ አንድ ፐርሰንት፡፡
- አነስተኛ የክሬዲት ስኮር፡ 660
- የዴት ቱ ኢንካም ሪሾ (ያለብዎት እዳ ከጠቅላላ ገቢዎ አንጻር)፟ 45%
- ዋና አበዳሪ መገኘቱን የሚያረጋግጥ ሰነድ (ይህ ከወለድ ነጻ ብድር የሚፈቀደው ተበዳሪዎች አስቀድመው የሚያስፈልጋቸውን አበዳሪ ካገኙ በሗላ ነው)
በዚህ ዕድል ለመጠቀም ወይንም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ፡፡