@ethiopique202-1

በመጀመሪያ ዙር የፕሬዘደንትነት ዝመናቸው በሙስሊም ሀገራት ላይ ባወጁት የጉዞ እግድ ወቀሳ የቀረበባቸው ፕሬዘደንት ትራምፕ አሁን ደሞ ኤርትራና ሱዳንን ጨምሮ በ43 አገራት ዜጎች ላይ በ3 እርከን የተከፋፈለ የጉዞ እግድ ረቂቅ አቅርበዋል::

ይህ ረቂቅ ሀገራት በቀይ በብርቱካናማና በቢጫ ይከፍላቸዋል:

በቀይ የተመደቡት አገራት 11 ሲሆኑ እነሱም አፍጋኒስታን; ቡታን; ኩባ; ኢራን; ሊቢያ; ሰሜን ኮርያ; ሶማልያ; ሱዳን; ሶርያ; ቬንዙዌላና የመን ይገኙበታል::

እነዚህ በቀይ ቀለም ምድብ የሚገኙ አገራት ዜጎች በፍፁም ወደአሜሪካ እንዳይመጡ ተከልክለዋል::

በብርቱካናማ ቀለም ምድብ ውስጥ ደሞ አስር አገራት የሚገኙ ሲሆን የነዚህ 10 አገራት ዜጎች ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ ለመግባት ባይከለከሉም ወደ አሜሪካ ለመሄድ ያለው እድል እንዲቀንስና አመልካቾች ላይ ጥብቅ ምርመራ እንዲደረግባቸው ረቂቁ ያዛል::

በቢጫ ቀለም ስር በሶስተኛ ደረጃ ያሉት አገራት ዜጎች ለአሁኑ ምንም ክልከላ ባይኖርባቸውም የአሜሪካ መንግስት ግን አገራቱ ማስተካከል አለባቸው ያላቸውን ጉዳዮች በ60 ቀናት ካልተስተካከለ ደረጃቸው ከፍ እንደሚልና ቪዛ እንደሚከለከሉ ታውቋል::

በዚህ ምድብ ያሉ አገራት ደሞ የሚከተሉት ናቸው:: አንጎላ; እንታጋና ባርባዷ; ቤኒን; ቡርኪናፋሶ; ካምቦዲያ; ካሜሩን; ኬፕ ቨርዴ; ቻድ; ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ; ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ; ዶሚኒካ; ኢኳቶሪያል ጊኒ; ጋምቢያ; ላይቤርያ; ማላዊ; ማሊ; ሞሪታንያ; ሴንት ኪትስና ኔቪስ; ሴንት ሉቺያ; ሳኦ ቶሜና ፕሪንቺፔ; ቫናቱና ዚምቧቤ ይገኙበታል::

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.