
ነዋሪነታቸው በአሌክሳንድርያ ከተማ የነበረውና የቀድሞዋ በዩናይትድ ስቴትስ ምስራቃዊ ቨርጂንያ አቃቤ ህግ የነበረችው ጄሲካ አበር በድንገት ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በርካታ መላምቶች እየተንሸራሸሩ ይገኛሉ።
የአሌክሳንድርያ ፖሊስ እንዳስታወቀው ከሆነ አቃቤህጓ ባሳለፍነው ቅዳሜ ማርች 22 ጧት 9፡00 ሰዓት አቅራቢያ በ900 ቤቨርሊ ድራይቭ አቅራቢያ በድናቸው እንደተገኘና የሞታቸው መንስኤ ለማወቅ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ እንደሆነም ተነግሯል።
ጄሲካ አበር በቀድሞው የባይደን አስተዳደር በአቃቤህግነት ዘመኗ በርካታ ከፍተኛ ክሶትችን በማቅረብ ትታወቅ የነበረ ሲሆን በዋናነት ተጠቃሽ የሆኑት በሩስያ ዜጎች ላይ የነበሩት ክሶቿ ነበሩ። የክስ ዶሴዎች እንደሚያሳዩት ጄሲካ አበር ከዚህ ቀደም በዩክሬን በነበረው ጦርነት አሜሪካዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ላይ ፈጽመዋል በተባለው ወንጀል አራት የሩስያ ወታደሮች በጦር ወንጀል ለፍርድ አቅርባ በ2023 ያስፈረደች ሲሆን ሌሎች ሁለት ራሻውያንን ደሞ በህገወጥ የበርካታ ቢልየን ዶላር የገንዘብ ዝውውር ከሳ እንዲሁ አስፈርዳባቸው ነበር።
ጄሲካ አበር የአሁኑ ፕሬዘደንት ትራምፕ ወደስልጣን በመጡበት ወቅት የስራ መልቀቂያ አስገብታ ከመንግስት ስራዎ በፍቃዷ ለቃ የነበረ ሲሆን ይህም በወቅቱ ፖለቲካዊ ጫና ደርሶባት ሊሆን እንደሚችል መላምቶች ነበሩ። ድንገተኛ የሆነው አሟሟቷም ከዚህ ስራዋ ጋር የተያያዘ ይሆን የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ነው።
የጄሲካን ህልፈት ተከትሎ የዩ ኤስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሆኑት ፓም ቦንዲ የሀዘን መልዕክታቸውን ልከዋል። አሟሟቷ እጅግ የሚያሳዝን እንደሆነና በልባቸውና በጸሎታቸው እንደሚያስቧት ለወዳጅ ዘመድም መጽናናትና እንዲያገኙ እንደሚጸልዩ አስታውቀዋል።
የቨርጂንያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጄሰን ሚያሬዝም እንዲሁ ማዘናቸውን አስታውቀው ለወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ተመኝተዋል።
የአሌክሳንድርያ ፖሊስ ማክሰኞ 3/25 ይህን መግለጫ አውጥቷል
