@ethiopique202 (54)

በማርች ወር አጋማሽ ሰለሞን አራያ በሚያሽከረክረው ከባድ መኪና ምክንያት በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት የተቀጠፈ ሲሆን ይህን ተከትሎም የቴክሳስ ፖሊስ በወቅቱ ተጠርጣሪ ያለውን ሰሎሞን አራያ ጠጥቶ ወይንም በተጽዕኖ ውስጥ ሆኖ በማሽከርከር ወንጀል ከሶት ነበር።

ፖሊስ ለዚህ ምክንያት ያለው ደሞ በወቅቱ ሰለሞን ሲንገዳገድ የነበረ በመሆኑና ቃላትን አሰካክቶ መናገር አልቻለም በሚል ምክንያት ነበር።

ሆኖም ከሳምንታት በኋላ የሰለሞን የደምና የሽንት ምርመራ በውስጡ ምንም አልኮል እንዳልነበር ያሳየ መሆኑን ተከትሎ የተጠርጣሪው ጠበቃ ክሱ እንዲሻሻል፤ የዋስ ማስያዣውም ዝቅ እንዲልና ደንበኛቸው ጉዳዩን ከውጭ ሆነው እንዲከታተል አቤቱታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በዚ አቤቱታ በመስማማት የማስያዣውን ገንዘብ መጠን ወደ 7000ዶላር ዝቅ አድርጎታል።


ይህንን ተከትሎም ሰለሞን አራያ ትላንት ኤፕሪል 30 በዋስ የተጠየቀውን ገንዘብ አስይዞ ከእስር ወጥቷል። ጉዳዩንም በውጭ ሆኖ ይከታተላል ተብሏል።

የአቃቤ ህግ እንዳሳወቀው ከሆነም ሰለሞን ጉዳዩ በፍርድ ላይ እያለ የንግድ መኪና መንዳት እንደተከለከለ ያስታወቀ ሲሆን ጉዳዩ እስኪያልቅም ከአገር እንዳይወጣ ፓስፖርቱንና ሌሎች ዶክመንቶችን እንደሚያስረክብ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሰለሞን በእግሩ ላይ ያለበት ቦታ ለፖሊስ የሚጠቁም የጂፒ ኤስ መከታተያ እንደሚያደርግና በየጊዜው በድንገት ለአደንዛዥ እጽ ወይም አልኮሆል መመርመሪያ ሽንት ናሙና እንደሚወሰድበት ተነግሯል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.