Screenshot 2025-05-06 at 11.10.59 AM

ባሳለፍነው አርብ ሜይ 2 የ2026 አመት በጀታቸውን ይፋ ያደረገው የትራምፕ ዋይት ሀውስ በርካታ የበጀት ቅነሳዎችን እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ ከነዚህም ዋነኞቹ የማህበረሰብ ጤና ላይ፤ የሀይል አቅርቦት ላይ፤ የትምህርት ድጋፍ ላይ፤ የቤቶች አቅርቦት ላይና አለም አቀፍ ተራድዖ ላይ ከፍተኛ የበጀት ቅነሳ እንደሚኖርና አብዛኛውን ድጋፍና ሀላፊነት ስቴቶች በባለቤትነት እንዲወስዱ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል፡፡ 

በዚህ የበጀት ዕቅድ ላይ ከተቀመጡት አንዱና ዋነኛው በቤቶችና በኪራይ ድጋፍ ላይ ያለው ተጠቃሽ ነው፡፡ እንደ ሴክሽን 8 የመሳሰሉ የፌደራል መንግስት የቤት ኪራይ ድጋፎችን በሚመለከት ወደ ስቴቶች እንዲዘዋወሩና ስቴቶች በባለቤትነት እንዲያስተዳደሩት የሚያዝ ሲሆን በእንደዚህ አይነት መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩና ባለሙሉ ጤና የሆኑ ሰዎች ከ2 አመት በላይ ለሆነ ጊዜ በዚህ የመንግስት ቤት መኖር እንደማይችሉ ያዛል፡፡ ይህ ድንጋጌ አሁን በመንግስት ድጋፍ በሚደረግላቸው ቤቶች የሚኖሩ ወይንም የቤት ቫውቸር የሚቀበሉ ሰዎችን ህይወት ሊያናጋው እንደሚችል ይገመታል፡፡ 
በዚህ ዕቅድ ላይ እንደተቀመጠው ከሆነ የፌደራልም ሆነ የስቴቶች የቤት ድጋፍ ለአዛውንቶችና የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች ብቻ ያለ ገደብ መሰጠት እንዳለብትና ሌላው ጤነኛው ህዝብ ግን በሁለት አመት ውስጥ ራሱን ችሎ መውጣት እንዳለበት ረቂቅ ሆኖ ቀርቧል፡፡

በዚህ ረቂቅ በጀት ላይ የቀረበው ሌላው የወጪ ቅነሳ ለነዋሪዎች የመብራትና የጋዝ ክፍያ ድጎማ ከፌደራል መንግስት ያቀርብ የነበረው የLIHEAP ፕሮግራም ሲሆን ይህ ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ እንዲቆምና ሀላፊነቱን ስቴቶች እንዲወስዱ ተጠይቋል፡፡ 

በጤናው ዘርፍ ደግሞ በሜሪላንድ ከሚገኙት ከናሽናል ኢንስቲትዩት ኦፍ ሄልዝ በጀት ላይ የ17.9  ቢልየን ዶላር ቅነሳ እንዲደረግ ሲጠየቅ ከሲዲሲ ደግሞ የ3ነጥብ6 ቢልየን ዶላር ቅናሽ ተጠይቋል፡፡ ሜክ አሜሪካ ሄልዚ አጌን ለሚለውና በሴክሬተሪ ኬኔዲ ለሚመራው ንቅናቄ ደሞ የ500 ሚልየን ዶላር ጭማሪ የተደረገ ሲሆን ይህ ንቅናቄ በዋናነት በሽታ መከላከል ላይና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን በስፖርትና በጤናማ ምግብ የመተካት ስራን ይሰራል ተብሏል፡፡ ስደተኞችን በጅምላ ከአሜሪካ ለማባረር እንዲረዳ፤ ደቡባዊን ድንበር የማጠር ስራ እንዲጠናቀቅና ለመሳሰሉ ጉዳዮች በሚል ደሞ የዲፓርትመንት ኦፍ ሆምላንድ ሴኩሪቲ የ43 ነጥብ 8 ቢልየን ዶላር ጭማሪ ተጠይቆበታል፡፡ በተጨማሪም በሜሪላንድ የሚገኘው ናሳ እንዲሁ ከፍተኛ የበጀት ቅነሳ ከተጠየቁባቸው ተቋማት አንዱ ነው፡፡ 

ይህ ረቂቅ በጀት በአለም አቀፍ ደረጃ አሜሪካ በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪና ሌሎች የመንግስታቱ ድርጅት አካል የሆኑ ተቋማት ዘንድ ያላትን መዋጮ በሰፊው የሚቀንስ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪዎች በተለያዩ አህጉራት የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውር ላይ እንደሚሳተፉና በተለይም በሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ እኚህ የሰላም አስከባሪዎች ወርቅ፤ አልማዝና አደንዛዥ ዕጽ አዘዋውረዋል ሲል የትራምፕ ዋይት ሀውስ በረቂቁ ላይ አስፍሯል፡፡ በተጨማሪም ከአፍሪካ ዴቨሎፕመንት ባንክ ላይ የ555 ሚልየን ዶላር ቅናሽና ከምግብ ለሰላም ፕሮግራም ላይ የ1ነጥብ 6 ቢልየን ዶላር ቅናሽ እንዲደረግ ሀሳብ ቀርቧል፡፡ 
በጀቱ በአብዛኛው ለስደተኞች ይደረጉ የነበሩ የቋንቋና ሌሎች ክህሎት ስልጠናዎችን ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ እንዲቋረጡ ያዛል፡፡ 

የመከላከያ በጀት በ113 ነጥብ ሶስት ቢልየን ዶላር ጭማሪ ከሁሉም በላይ ከፍተኛ ጭማሪ የተጠየቀበት ዲፓርትመንት ሲሆን ብቸኛው ምንም የበጀት ቅናሽ የሌለው ዲፓርትመንትም ነው፡፡ ሌላው ከፍተኛ የበጀት ጭማሪ የታየው በዲፓርትመንት ኦፍ ትራንስፖርት በቀጣይ ወራት ኮንግረስ ይህን ረቂቅ በጀት እንደሚመረምርና ወሳኔውን እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡ ኢትዮጲክ እንደተለመደው ተከታትላ ውሳኔውን ታሳውቃለች፡፡ የዋይት ሀውስን ሙሉ የበጀት ረቂቅ ለማየት ይህን ይጫኑ፡፡ 

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.