@ethiopique202 (73)

በጆርጂያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፐሪሜትር ኮሌጅ በኢንጂነሪንግ ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ለመያዝ እየሰራች ያለችው ራኬብ ተስፋስላሴና ፓሎማ ሆጅ በአገሪቱ ትልቅ ክብር ያለውን የጃክ ኬንት ኩክ ፋውንዴሽን ስኮላርሺፕ አሸናፊ ሆነዋል።

ይህ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም ለተማሪዎቹ በአመት እስከ 55ሺህ ዶላር ድረስ የትምህርት ወጪያቸውን መሸፈን የሚያስችላቸውን ድጋፍ ያደርጋል።

ራኬብ በ2024 በነበረው የኮሚውኒቲ ኮሌጅ ኢኖቬሽን ቻሌንጅ ላይ ከሁለት ጉዳኞቿጋ ተወዳደራ በሰሩት ሴቶች በራሳቸው የፓፕ ስሚር (ለሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ) ናሙና መውሰድ በሚችሉበት ግኝት ውድድሩን አሸንፋ ነበር።

ፓፕ ስሚር የማህፀን ጫፍ (በር) ካንሰርን (Cervical Cancer) ለመለየት የሚጠቅም ወሳኝ ምርመራ ነው።

የፓፕ ስሚር ምርመራ በማህፀን በር ጫፍ ውስጥ ያሉ ያልተለመዱ ህዋሶችን መለየት ይችላል፣ ይህም የማህፀን በር ካንሰርን የመጀመሪያ ምልክቶች ይጠቁማል፡፡ መደበኛ የፓፕ ስሚር ምርመራ የማህጸን በር ካንሰርን ቀደም ብሎ ለመለየት እና ቶሎ ህክምና ለማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው፣ ስለሆነም ዕድሜያቸው ከ21-65 ዓመት ለሆኑ ሴቶች በየ3 ዓመቱ ምርመራው እንዲደረግላቸው ይመከራል፡፡

ፓፕ ስሚርን ሴቶች አስቀድመው መመርመራቸው ካንሰርን ቀደም ብሎ ለመለየት ያግዛል፡፡ የማህፀን በር ካንሰር ቀደም ብሎ ሲታወቅ በቀላሉ ሊታከም ይችላል አሳሳቢ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ለመለየት ይረዳል።

የራኬብ ግኝትም ሴቶች በራሳቸው ናሙና መውሰድና ለምርመራ መላክ የሚቻልበትን ሀሳብ ይዘው ቀርበው አሸንፈዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.