WRAP_Cruiser_2020

የዋሽንግተን ሪጅናል አልኮሆል ፕሮግራም (WRAP) ሁሌም እንደሚያደርገው በመጪው የኢንዲፔንደንስ ዴይ/ጁላይ 4 / በዓል ላይ ሰዎች ሰክረው እንዳያሽከረክሩ በማሰብ ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ላሉ ቀምቃሚዎች እስከ 15$ ድረስ የሊፍት ሂሳብ ይከፍላል።

ከ15 ብር በላይ ሂሳብ ከመጣ ከ15$ በላይ ያለውን ተሳፋሪዎች ራሳቸው መክፈል ይኖርባቸዋል። ድርጅቱ እስካሁን ድረስ ለ80047 ሰዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጥቷል። ይህ ፕሮግራም በዋናነት ለገናና አዲስ አመት፤ ለሴይንት ፓትሪክስ ቀን፤ ለ ሲንኮ-ዴ-ማዮ፤ ለኢንዲፔንደንስ ዴይ/ጁላይ 4ና ለ ኃሎዊን የነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል። በዚህ የነጻ ትራንስፖርት እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ብቻ መጠቀም ይችላሉ።

የሊፍት ኮዶቹ ሰኞ ጁላይ 4 ከ 3፡00 pm ጀምሮ ይወጣል። ይህን ሊንክ ተከትለው በመሄድ የቅናሽ ኮዱን ማግኘት ይችላሉ። ኮዱ ለኡበር አይሰራም። ኮዱ ቀድመው ለመጡ ለመጀመሪያዎቹ 2200 ሰዎች ብቻ ነው የሚያገለግለው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.