01/10/2025
እንዲታገድ ተወሰነበት (4)

በ2025 የቨርጂንያ ነዋሪዎችና የንግድ ተቋማት በርካታ አዳዲስ ህጎች ያጋጥሟቸዋል። እነዚህን ህጎች አንድ በአንድ እነሆ

የዝቅተኛ ክፍያ ጭማሪ (ሚኒመም ዌጅ ጭማሪ)

ከጃንዋሪ 1 2025 ጀምሮ በቨርጂንያ በሰዓት ዝቅተኛው ክፍያ ቀድሞ ከነበረበት 12.00$ ወደ 12.41$ ከፍ ይላል። ይህ ሂደትም በ2026 የዝቅተኛ ክፍያ ዋጋን ወደ 15$ ከፍ እንዲል የተያዘው እቅድ አንድ አካል ነው።

ብሄር (ዘውግ) ጥበቃ የሚደረግለት መደብ ይሆናል

ልክ እንደ ጾታ፤ ዘር፤ አካል ጉዳትና የመሳሰሉት ሁሉ አንድ ሰው በብሔር ወይንም በዘውግ አማካኝነት አድልዖና መገለል እንዳይደርስበት የቨርጂንያ ሰብዓዊ መብት አዋጅ ደንግጓል። ይህንንም ተከትሎ ስራ ቀጣሪዎች የሰራተኞቻቸውን ስልጠናና ፖሊሲ ሲያዘጋጁ ይህን መብት እንዲያካትቱ ታዘዋል።

አዲስ የጡረታ ህግ ለቀጣሪዎች

በስራቸው ከ25 በላይ ሰራተኞች ያሏቸውና ለሰራተኞቻቸው ምንም አይነት የጡረታ ጥቅማጥቅም የማይሰጡ ቀጣሪዎች ከመጪው አመት ጀምሮ ሪታየር-ፓዝ ቨርጂንያ የተባልው የጡረታ ፕሮግራም ለሰራተኞቻቸው እንዲያቀርቡ የሚያስገድድ ህግ ተግባራዊ ይሆናል።
ሰራተኞች ራሳቸውን ከፕሮግራም ካላስወጡ በስተቀር በፕሮግራሙ እንደሚመዘገቡና ይህንን ያላደረጉ ቀጣሪዎች በአንድ ሰው እስከ 200$ እንደሚቀጡ ተነግሯል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *