የአዲሱ አመት መጀመርን አስመልክቶ አዳዲስ ህጎች በሜሪላንድ ተግባራዊ ይሆናሉ። አንዳንዶቹ ህጎች ልክ አመቱ ሲጀምር ጃንዋሪ 1 የሚጀምሩ ሲሆን የተወሰኑት ደሞ ቀስ ብለው ከወራትና ሳምንታት በኋላ ይጀምራሉ። እነዚህ ህጎች የሚከተሉት ናቸው።
የመስማት ችግር ላለባቸው የጆሮ ማዳመጫ (ሂሪንግ ኤይድ) ለአዋቂዎች
የጆሮ ማዳመጫ ለሁሉም አዋቂ በፍትሀዊነት እንዲዳረስ በማሰብ SB 778 የተባለው የሜሪላንድ ህግ የጤና ኢንሹራንስ ተቋማትና ሌሎች የጤና ድርጅቶች በየ36 ወራቱ እስከ 1400$ ድረስ ለሂሪንግ ኤይድ መግዣ እንዲፈቅዱ ተደንግጓል።
የሴኪውሪቲ ጋርድ ፍቃድ
ከጃንዋሪ 1 2025 ጀምሮ በጤና ተቋማት የጥበቃ ባለሞያዎችን የሚቀጥሩ ድርጅቶች በየሳምንቱ መረጃዎችን ለሴክረታሪ ኦፍ ስቴት ፖሊስ እንዲያስገቡ ይደነግጋል። ይህም በሴኪውሪቲ ሙያ ያለውን ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖር ያደርጋል ተብሏል።
So Every Body Can Move Act: (ሁሉም ሰው እንዲንቀሳቀስ)
ይህ ህግ በተለይም የተወሰኑ የጤና ኢንሹራንስ ድርጅቶችና የሜሪላንድ የህክምና ድጋፍ ፕሮግራም ለአርቴፊሻል የሰውነት ክፍሎች (prostheses) የኢንሹራንስ ሽፋን እንዲሰጡ ያስገድዳል።
ከመጠን በላይ የእጽ ህግ (Opioid Overdose and Opioid–Related Emergency Medical Conditions – Treatment:)
ይህ ህግ የሜሪላንድ ሆስፒታሎች በሰውነታቸው ከፍተኛ የኦፒዮይድ መጠን የተገኘባቸውን ሰዎች የሚያክምበትን መንገድ እንዲያዘጋጁና በዛ ፕሮቶኮል መሰረት እንዲተገብሩ ያዛል። በዚህ አዲስ ህግ መሰረትም ከኦፒዮይድጋ በተያያዘ የሚመጡ ታማሚዎችን ከሆስፒታል መልስ ሌላ ድጋፍ እንዲያገኙ ወደ ሌሎች የድጋፍ ፕሮግራሞች እንዲልኳቸው ያዛል። ይህም ያልተቋረጠ ድጋፍ እንዲያገኙና እንዲያገግሙ ያግዛል።