የቀድሞ ፕሬዘደንቶች ከሞቱበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት የዩናይትድ ስቴትስ ሰንደቅ አላማ በግማሽ እንዲውለበለብ የፌደራል ህጉ ያዛል። ይህን ተከትሎም የቀድሞው ፕሬዘደንት ጂሚ ካርተርን ዜና እረፍት አስታከው የሜሪላንድና የዲሲ መንግስታት ሰንደቅ አላማዎቻቸው እስከ ጃንዋሪ 28 በግማሽ እንዲውለበለቡ አዘዋል። የቨርጂንያ መንግስት እስካሁን ይህን አላስታወቁም። ድረ-ገጻቸው ላይ እስከ ሰኞ ዲሴምበር 30 2024 ድረስ ባንዲራዎች በሙሉ ባሉበት እንዳሉ ያሳያል።