ዲሴምበር 30, 2024– የዲሲ ከንቲባ ከመጪው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘደንትጋ እንደተወያዩና ሁለቱም ለዲሲ መልካም ነገሮችን እንደሚፈልጉ; ከተማው ከአለም ውብ ከተሞች ተርታ እንድትመደብና የአሜሪካንን ጥንካሬ ማሳያ እንድትሆን እንደሚፈልጉ ባወጡት መግለጫ ከንቲባዋ አስታውቀዋል::
የከተማው አስተዳደርና የፌደራል መንግስት አብረው መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ በተለይም የፌደራል መንግስት ሰራተኞችን ወደስራ መመለስ በተመለከተ; በአግባቡ ጥቅም ላይ ያልዋሉ የፌደራል ህንፃዎችንና ፓርኮችና መናፈሻዎችን በሚመለከት እንደተወያዩ ዛሬ ምሽት ባወጡት መግለጫ ከንቲባዋ አስታውቀዋል::