01/09/2025
GgTBfAxXQAAxNtc

Image Credit: US Capitol Police

ሐሙስ ጃንዋሪ 2 2025 – ዋሽንግተን ዲሲ 

ዛሬ ጧት 10 ሰዓት ላይ የካፒቶል ፖሊስ አባላት በዲሲ ዳውንታውን ፒስ ሰርክል በኩል ወደ ሰርድ ስትሪትና በኮንስቲቱሽን አቬኑ አቅራቢያ ባለ የእግረኞች መንገድ ላይ አርጎ ወደ ሳር ላይ መኪና እየነዳ የገባ አሽከርካሪ አግኝተው በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት አስታውቀዋል፡፡ የካፒቶል ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ በመኪናው ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝና በሚከተሉት መንገዶች ለአሽከርካሪዎችም ሆነ ለእግረኞች ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው በፖሊስ ሲወሰድ የሚያሳይ ነው የተባለ ቪዲዮም በሰቨን ኒውስ ጋዜጠኛ ብራድ ቤል ትዊተር ላይ ተለቋል፡፡

የካፒቶል ፖሊስ 11:43am ላይ መኪናውን ፈትሾ ቦንብም ሆነ ሌላ ጉዳት የሚያደርስ ነገርእንዳላገኘ ገልፇል:: ተጠርጣሪው በግዴለሽ ማሽከርከር እንደሚታሰርም አክለው ገልፀዋል::

የካፒቶል ፖሊስ ከሰአት ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ተጠርጣሪው የ26 አመትእድሜ የጆርጂያ ነዋሪ የሆነው ሀሪ ቻናሞሉ እንደሆነ ይህ ግለሰብም የቴሌኮሚኒኬሽን ሰራተኛ እንደሆነና በሰአቱ በአካባቢው በስራ ላይ እንደነበረ አስታውቋል::

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *