ከቨር.zip - 1-1

የአርሊንግተን ፖሊስ አቶ ተኪዬ ተገኝተዋል ብሏል:: መረጃውን ላጋራችሁ በሙሉ እናመሰግናለን::

የአርሊንግተን ፖሊስ ዛሬ ባወጣው የአፋልጉኝ ጥሪ የ67 አመት አዛውንት የሆኑትን አቶ ተኪዬ ተስፋማርያምን ያያችሁ ጠቁሙኝ ብሏል፡፡ እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ አቶ ተኪዬ ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ንጋት 6፡30am ላይ ሲሆን በ3700 ላንግስተን ቡሌቫርድ አቅራቢያ እንደሆነና በሰዓቱም ፈካ ያለ ቡናማ (Tan) ጃኬትና ግራጫ ቱታ አርገው እንደነበር ተናግሯል፡፡ 

የአርሊንግተን ፖሊስ በከፋ አደጋ ላይ ሊገኙ ይችላሉ ያላቸው እኚህ አዛውንት የአዕምሮ ጤና እክል ያለባቸው በመሆኑ እንደሆነም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡ አቶ ተኪዬ ያሉበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር 703-558-2222 ወይንም በ 911 እንዲደውልና እንዲያሳውቅ ፖሊስ ጠይቋል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.