
በቀኝ ዘመም ፖለቲከኞችና ደጋፊዎች ዘንድ በምስጢራዊነቱ ለበርካታ መላምቶች መነሻ የሆነው የጄፍሪ ኤፕስቲን የጉዞ ዝርዝርና ሌሎች መረጃዎችን የያዙ ዶሴዎችን የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፓሜላ ቦንዲ ከኤፍ ቢ አይ ጋ በመሆን ዛሬ ለህዝብ ይፋ አድርገዋል።
በዚህ ዙር ይፋ የሆኑት መዝገቦች በዋናንነት የበረራ መዝገብና የሰዎች አድራሻ መዝገብ ናቸው።
በወሲባዊ ትንኮሳ ወንጀለኛ ተብሎ የተፈረደበት ኤፕስቲን ከ250 በላይ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሴቶችን በማባለግና ለሌሎች አሳልፎ በመስጠት ወንጀል ተፈርዶበት በእስር ላይ እንዳለ ራሱን አንዳጠፋ ይታወቃል።
የዩ ኤስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፓሜላ ቦንዲ የኤፕስቲን ዶሴዎችን በሙሉ እንዲሰጧቸው ለኤፍ ቢ አይ ባለሟሎች እንደጠየቁና አስካሁን 200 ገጽ ብቻ እንደተሰጣቸው ሆኖም ኒው ዮርክ በሚገኘው የኤፍቢ አይ ቢሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶሴዎች እንዳሉና በአስቸኳይ ለህዝብ ይፋ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።
የዩ ኤስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፓሜላ ቦንዲ ቀሪ የኤፕስቲን ኤግዚቢቶች በሙሉ እስከ ነገ ፌብሯሪ 28 8am ተጠቃለው እንዲደርሷቸው የኤፍ ቢ አይ ዳይሬክተር የሆኑትን ካሽ ፓቴልን በደብዳቤ ጠይቀዋል። እስካሁን ለምን እንዳልተሰጣቸውም ምርመራ እንዲደረግ አዘዋል።
እስካሁ የተለቀቁ የኤፕስቲን ዶሴዎችን ለማየት ይህን ይጫኑ።
