img_0282-1

ባለፈው ሳምንት በዲሲ ፖሊስ ተተኩሶበት ለህልፈት የተዳረገው የሱራፌል አባት አቶ አበባው ከሰሞኑ በተዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍና የሱራፌል መታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ይህንን ብለዋል።

እንደ አባትዬው ገለጻ ሱራፌል በሰዓቱ የለበሰው ጭምብል የብርድ መከላከያ እንደሆነና የፖሊስ ሪፖርት ፍጹም ውሸት እንደሆነ ተናግረዋል። ፖሊሶች ከኋላ ተከታትለው የመጀመሪያው አንድ ተመቶ እያነከሰ እያለ በቴዘር መምታት ሲችሉ ሌላ 13 ጥይት ተኩሰው ነው የገደሉት ያሉ ሲሆን አክለውም ሱራፌል የመጠጥም ሆነ የአደንዛዥ እጽ አመል እንደሌለበት ተናግረዋል። የዲሲ ፖሊስ የቦዲ ካሜራ ይፋ ከሆነ በኋላ በበርካታ የኢትዮጲክ አንባቢዎች ዘንድ የፖሊስ እርምጃ ፍትሀዊነት ጥያቄ ውስጥ ገብቶ ነበር።

በቀጣይም የፖሊስ ከልክ ያለፈ ሀይል መጠቀምን በመቃወም ወደህግ ሊወስዱ እንዳሰቡና ለዚህ እንዲረዳቸውም የጎ ፈንድ ሚ መዋጮ እንዳዘጋጁና ማህበረሰቡ በገንዘብም በሀሳብም እንዲደግፋቸው ጠይቀዋል። በተጨማሪም የሱራፌል ታሪክ እንዲታወስና ፖሊስ ተጠያቂ እንዲሆን እንደሚታገሉ በጎ ፈንድ ሚ ገጹ ላይ አስገንዝበዋል። በዚህ ጎ ፈንድ ሚ ላይ የአቶ አበባውን ቤተሰብ ለመርዳት ከፈለጋችሁ ይህንን ሊንክ ተጭነው ይለግሱ።

የዲሲ ፖሊስ ከዚህ ቀደምም አላግባብ ከልክ በላይ የሆነ ሀይል በመጠቀም የሰው ነፍስ አጥፍቷል ተብሎ ተከሶ እንደነበር በሴፕቴምበር 2024 መዘገባችን ይታወሳል። በወቅቱ በሳውዝ ኢስት ዲሲ የማክዶናልድ ምግብ ቤት አቅራቢያ በፖሊስ ተተኩሶበት ለህልፈት የተዳረገውና በዲሲ ወንጀልን (ሁካታን) ለመቀነስ ይሰራ የነበረውን ጀስቲን ሮቢንሰን የተባለ ወጣትን ተኩሰው ሲገድሉ የሚያሳየው ቪዲዮ በዲሲ ፖሊስ ለህዝብ ይፋ ከሆነ በኋላ በዲሲ አንዳንድ አካባቢዎች ረብሻ እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱ የኢትዮጲክ ባልደረቦች ያነጋገሯቸው የሳውዝ ኢስት ነዋሪዎች ልክ እንደ አቶ አበባው ጀስቲንን የሚያውቁት ሰዎች ይህ እንደማይገባውና ጥፋተኛው ፖሊስ ነው ብለው ነበር።

@yared.dmvethiopia

#duet with @Dani Prank #ethiopian #LIVE gofund.me link https://gofund.me/75c18fc1

♬ original sound – Dani Prank

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.