IMG_9882

በዲሲ የቅጥር አገልግሎት ዲፓርትመንት የሚተዳደረው ከንቲባው ማሪዮን ኤስ.ባሪ የበጋ የወጣቶች ሥራ ስምሪት ፕሮግራም (MBSYEP) ከ14 እስከ 24 ዓመት የሆናቸው የዲስትሪክቱ ወጣቶች በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ ድጎማ በሚደረግላቸው ምደባዎች የሰመር ሥራ ልምድ እንዲያገኙ ታስቦ ከ46 ዓመት በፊት የተጀመረ ፕሮግራም ነው።
በዚህ ፕሮግራም በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ታዳጊዎች በተለያዩ ዘርፎች ባሉ ተቋማት በመግባት እንዲሰሩ የሚያችላቸው ሲሆን በስራ አለም ካለው ህይወትጋ እንዲተዋወቁ በር ከፋች እንደሆነ ተነግሯል። በ2024 ሰመር 12000 ያህል ታዳጊዎችና ወጣቶች በ800 የሚጠቅጉ ቀጣሪዎች አማካኝነት በዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንደነበሩ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ጠቁመዋል።

ከወትሮው በተለየ ዘንድሮ አዲስ ፕሮግራም የሚጀመር እንደሆነና ይህም በፋይናንስ ላይ ያተኮረ የልምድ ማስጨበጫ ምደባ እንደሆነም የዲሲ ከንቲባ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በዚህ ልዩ ፕሮግራም በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪ የሆኑና ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 18 የሆኑ ታዳጊዎች ብቻ የሚሳተፉበት ይሆናል። ቀጣሪዎች በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ እስከ ጁን 1 ማመልከቻቸውን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ተማሪዎች ደሞ እስከ ማርች 6 2025 ማመልከቻቸውን ማስገባት ይችላሉ።

ይህ የታዳጊዎች የስራ ቅጥር ፕሮግራም ምዝገባ ከዛሬ ጃንዋሪ 27 2025 እስከ ማርች 6 2025 የሚካሄድ ሲሆን በፕሮግራሙ መሳተፍ የሚችሉት ደሞ የዲሲ ነዋሪ የሆኑና እድሜያቸው ከ14-24 የሆኑ ታዳጊዎችና ወጣቶች ናቸው። የስራ ቅጥር ፕሮግራሙ ከጁን 24 2025 እስከ ኦገስት 2 2025 ይከናወናል።
ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ እድሜያቸው ከ9 እስከ 13 ለሆኑ ታዳጊ የሚድል ስኩል ተማሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ የሆነው Career Ready Early Scholars Program (CRESP) ፕሮግራም ተከፍቷል ሲሉ ከንቲባዋ በመግለጫቸው አስታውቀዋል። በዚህ አዲስ ፕሮግራም እድሜያቸው ከ9-13 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ተብሏል። ለተሳታፊ ታዳጊዎቹ አጠቃላይ በሆኑ የስራና ሙያ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል ፕሮግራም ነው ተብሏል።

የወጣቶችና ታዳጊዎች የበጋ ስራ ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.