
የአርሊንግተን ካውንቲ የዲጂታል እኩልነት ፕሮግራም በፌብሯሪ 18 ለሚጀምረው የመሰረታዊ ኮምፒውተር ትምህርት ምዝገባ ጀምሯል። ትምህርቱ ከፌብሯሪ 18-20፤ 2025 በአርሊንግተን ሚል ኮሚውኒቲ ማዕከል (Arlington Mill Community Center፣ Room 503. 909 S. Dinwiddie St. Arlington, VA 22204) ይሰጣል።
ይህ የትምህርት ፕሮግራም ለተሳታፊዎች በነጻ የሚሰጥ ሲሆን አስተማሪዎች በእንግሊዝኛና በስፓኒሽ ቋንቋ ያስተምራሉ።
በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ይህንን ሊንክ በመጫን፤ በኢሜይል digitalequity@arlingtonva.us ወይንም በስልክ ቁጥር 703-228-3536 በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
ስለ ፕሮግራሙ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ።
የትምህርቱ መርኃግብር ይህን ይመስላል።