
የአሜሪካ መከላከያ ከትላንት በስትያ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ወቅት ሄሊኮፕተሩ ላይ የነበሩትን የሁለት ወታደሮች ማንነት ይፋ ያደረገ ሲሆን የሶስተኛውን ወታደር ማንነት በቤተሰቦቻቸው ጥያቄ አማካኝነት ይፋ እንደማያደርግ አስታውቋል።
በሄሊኮፕተሩ ላይ እነማን ነበሩ?
አንድሩ ሎይድ ኢቭስ

ቺፍ ዋራንት ኦፊሰር 2 አንድሩ ሎይድ ኢቭስ የ39 አመት የሄሊኮፕተር ፓይለት ሲሆን የግሬት ሚልስ ሜሪላንድ ነዋሪ ነበር። የአንድሩ ኢቭስና የሌላ ባልደረባው አስከሬን እስካሁን አልተገኘም።
አንድሩ ኢቭስ በዩ ኤስ ኔቪ (ባህር ኃይል) ውስጥ ለ10 ዓመታት አገልግሎ በ2017 ወደ አርሚ (መከላከያ) በመግባት የUH-60 (ብላክ ኃውክ ሄሊኮፕተር) ፓይለት ሆኗል።
በስራ ዘመኑ ሁሉም በርካታ ሽልማቶችን ተቀዳጅቷል። ከሽልማቶቹ መኃል ተጠቃሾቹም Army Commendation Medal (ሶስት ጊዜ), የNavy Commendation Medal, የArmy Achievement Medal, እና የNavy Achievement Medal (ሶስት ጊዜ) ነበሩ።
ራያን ኦስቲን ኦ’ኃራ

ስታፍ ሰርጀንት ራያን ኦኃራ የ28 ዓመት ወጣት የሊልበርን ጆርጂያ ነዋሪ ነበር። ይህ ወታደር እስካሁን ሬሳው አልተገኘም።
ሶስተኛው በሄሊኮፕተሩ ላይ የነበር ወታደር ግን በቤተሰቦች ጥያቄ ምክንያት ማንነታቸው አይገለጥም ተብሏል።
ወታደሮቹ በወቅቱ የምሽት ስልጠና ላይ እንደነበሩም ተገልጿል። የግጭቱ መንስኤ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።
የመርማሪ ቡድኑ ዛሬ አርብ ጃንዋሪ 31 2025 እንዳሳወቀው ከሆነ እስካሁን የ41 ሰዎች ሬሳ የተገኘ ሲሆን የሀያስምንቱ ማንነት ታውቋል።