
አደጋውን በመመርመርና የአስከሬን ፍለጋው ላይ የተሰማሩት የተባበሩት የድንገተኛ አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በመንገደኞች አውሮፕላን ላይ የነበሩት 67 ሰዎች አስከሬን የሁሉም እንደተገኘና የ66ቱ ማንነት በአግባቡ እንደታወቀ አስታውቀዋል፡፡
ይህም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ትልቅ ዕረፍት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ በመግለጫው ላይም በዚህ ፍለጋ ላይ የተሰማሩትን የዲሲ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች፤ የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት፤ የሜትሮፖሊታን ዋሽንግተን ኤርፖርቶች ባለስልጣን ፖሊስና የእሳት አደጋ ዲፓርትመንት፤ በዲሲና አካባቢው በሙሉ ያሉ የፖሊስና የእሳት አደጋ ተከላካይ ዲፓርትመንቶች፤ የዩ ኤስ አርሚ ኮር ኦፍ ኢንጂነርስ፤ የ ዩ ኤስ ኔቪ ሱፐርቫይዘር ኦፍ ሳልቬጅ እና ዳይቪንግ እንዳ የዩኤስ ኮስት ጋርድን የነበራቸው ብቃት በማድነቅ አመስግነዋል፡፡
የቺፍ ሜዲካል ኤግዛማይነር ቢሮ ስራውን እንደሚቀጥልና ሁሉም አስከሬን በአግባቡ ማንነቱ እንዲለይ እንደሚሰራ ታውቋል፡፡ የአስከሬን ማንነት የመለየት ስራው በመጠናቀቁም በቀጣይ የአውሮፕላኑን ስብርባሪዎች የመፈለግ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡
ማህበረሰቡም በፖቶማክ ወንዝና በአናኮስትያ አካባቢ የአውሮፕላኑን ስብርባሪዎች ካየ በፍጹም ከውሃ ውስጥ ለማውጣትም ሆነ ለመንካት እንዳይሞክሩና ይልቅስ በፍጥነት ወደፖሊስ እንዲደውል ተናግረዋል፡፡


