fairfax police-1

በፌርፋክስ ካውንቲ የፍራንኮኛ ፖሊስ ጣቢያ ዛሬ ማክሰኞ ፌብሯሪ 4 የወጣው ዜና እንደሚያሳየው በጃንዋሪ 27 ለሊት 2፡30am ላይ በ6700 block of Metropolitan Center Drive አቅራቢያ ወደቤቷ በመጓዝ ላይ እያለች ማምንነቱን የማታቀው ሰው እንደቀረባትና እንዳናገራት እንዲሁም በጉልበት አስገድዶ ሊደፍራት እንደሞከረ በፖሊስ መግለጫ ተገልጿል፡፡

ተበዳዩዋ በትግል ራሷን አስለቅቃ በመሮጥ ያመለጠች ሲሆን በሰዓቱ የተደወለላቸው ፖሊሶችም አካባቢውን ቢፈልጉ ተጠርጣሪውን ሊያገኙት አልቻሉም ነበር፡፡ ተበዳይዋ በወቅቱ አነስተኛ የሰውነት ጉዳት ደርሶባት ነበር፡፡

Yapheth Ably Emiru Photo Credit: Fairfax County Police

በወቅቱ የወንጀል ምርመራውን እንዲያደርጉ የታዘዙት የከባድ ወንጀል ቢሮ ባልደረቦችም ከተበዳይ ባገኙት መረጃ መሰረት የተጠርጣሪውን ፊት በምስል በማስቀረት ባደረጉት ምርመራ ወንጀሉን ፈጽሟል ያሉትን በዳይ የ30 አመት እድሜ ያለው የስፕሪንግፊልድ ነዋሪው ያፌት አቢይ እምሩ እንደሆነ እንደደረሱበትና በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት አስታውቀዋል፡፡

ያፌት በፌብሯሪ 2 2025 ወሲባዊ ጥቃት ለማድረስ በማገት፤ ያላግባብ ሰውን በመከታተል እንዲሁም በአስገድዶ የመድፈር ሙከራ ወንጀሎች ተጠርጥሮ የተከሰሰ ሲሆን ያለ ዋስትና ወደ ፌርፋክስ ካውንቲ የአዋቂዎች እስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

ለተበዳይም ባለሞያዎች ተመድበውላት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉላት እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ በዚህ ምርመራ ላይ ተጨማሪ መረጃ አለኝ የሚል ሰው በስልክ ቁጥር  703-246-7800 ደውሎ 3 ቁጥርን በመንካት መረጃውን ማስተላለፍ እንደሚችል ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ማንነታቸውን ሳያሳውቁ ጥቆማ ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች በስልክ ቁጥር 866-411-8477 ወይንም በኦንላይን በዚህ ሊንክ ጥቆማቸውን መስጠት ይችላሉ፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.