
ከኮቪድ 19 ፓንደሚክ በኋላ በርካታ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ከቤታቸው ይሰሩ የነበረ ሲሆን ፕሬዘደንት ትራምፕ ወደስልጣን መተው ባወጡት አዲስ ህግ መሰረት አብዛኛዎቹ ከነገ ሰኞ ፌብሯሪ 10 2025 ጀምሮ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኙ በርካታ የፌደራል ቢሮዎች በአካል በመገኘት ስራቸውን የሚሰሩ ይሆናል።
ይህን ተከትሎም ከዚህ ቀደም ብዙም መጨናነቅ ያልነበረባቸው የሜትሮ ባቡሮችና ባሶች ሊጨናንቁ እንደሚችሉ ተገምቷል። በተጨማሪም ከ16ሺ ያህል ሰራተኞች ውስጥ ከ8ሺህ እስከ 10ሺህ የሚገመቱት የራሳቸውን መኪና ይዘው ወደከተማዋ በተለይም ኔቪ ያርድ በሚባለው ሰፈር ባሉ የመኪና ማቆሚያዎች ለመገልገል እንደሚመጡ ይጠበቃል። የአካባቢው የፓርኪንግ የመያዝ አቅም እስካሁን 4473 ብቻ በመሆኑም የትራፊክ መጨናነቁ የማይቀር እንደሆነ ይጠበቃል ሲሉ የዋርድ 6 ካውንስል አባል ቻርልስ አለን አስታውቀዋል።

ይህን ተከትሎም የትራፊክ መጨናነቅ ሊፈጠር እንደሚችልና የመኪና ማቆሚያ ቦታ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ተገምቷል።
ነዋሪዎች ይህን አገናዝበው እንዲንቀሳቀሱና አስፈላጊ ከሆነም በጊዜ መንገድ እንዲጀምሩ ተመክሯል።