
የውሀ አፍሉ ማስጠንቀቂያው በ2/12/2025 ተነስቷል!
የፕሪንስ ጆርጅ ውሃ ስራዎች ድርጅት የፈነዳ የውሃ ማስተላለፊያ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ ዛሬ ማክሰኞ ፌብሯሪ 11 በከፊል የደቡባዊ ፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ ነዋሪዎች ውኃ እንደማያገኙና የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች እንደሚዘጉ አስታውቋል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ የፈነዳው የውኃ ማስተላለፊያ እንዳልተገኘና ተቋሙ በፍለጋ ላይ እንዳለም ተጨምሮ ተገልትጿል።
በዚህም ምክንያት የሚዘጉ ትምህርት ቤቶች የሚከተሉት ናቸው።
- Andrew Jackson Academy
- Arrowhead ES
- Avalon ES
- Benjamin Foulois Creative and Performing Arts
- Benjamin Stoddart MS
- Bradbury Heights ES
- Carmody Hills ES
- César Chávez Dual Spanish Immersion
- Crossland HS
- Excel Academy PCS
- Francis Scott Key ES
- Highland Park ES
- Hillcrest Heights ES
- Imagine Lincoln PCS
- Imagine Morningside PCS
- Longfields ES
- Maya Angelou French Immersion
- North Forestville ES
- Overlook Spanish Immersion
- Panorama ES
- Princeton ES
- Samuel Chase ES
- Samuel P. Massie Academy
- Skyline Administration Building
- Suitland ES
- Suitland HS
- Tayac ES
- William Beanes ES
- William Hall Academy
በተጨማሪም በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች ውኃቸውን አፍልተው እንዲጠቀሙ ተመክሯል። በዚህ ወቅት ፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ ወይም የታሸገ ውሃ ብቻ ለሚከተሉት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡: ካውንቲው ተገቢውን የላቦራቶሪ ምርመራ አድርጎ የውኃውን ጤነኛነት እስኪያረጋግጥ ድረስም ነዋሪዎች የቧንቧ ውኃ ሳያፈሉ እንዳይጠቀሙ መክሯል።

በነዚህ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?
- በቧንቧ ውኃ የተሰሩ በረዶዎችንና ሌሎች መጠጦችን ያስወግዱ
- ውኃ ከቧንቧ ሲወርድ ቀለሙን ከቀየረ ንጹህ ውኃ መፍሰስ እስኪጀምር ቧንቧውን ከፍተው ይተዉት
- የታወቁ የሊድ ምንጮች ካሉ ቀዝቃዛ ውኃ ለሁለት ደቂቃ ያፍሡ
- ውኃውን ቢያንስ ለ1 ደቂቃ በደንብ ያፍሉትና አቀዝቅዘው ይጠቀሙ
- የቀዘቀዘውን ውኃ በንጹህና በተሸፈነ ማስቀመጫ ያኑሩት
በዚህ ወቅት ፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ ወይም የታሸገ ውሃ ብቻ ለሚከተሉት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡
- ለመጠጥ
- ጥርስ ለመቦረሽ
- ምግብ ለማብሰል እና ማዘጋጀት
- ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ለማጠብ
- የሕፃናት ፎርሙላ ለማዘጋጀት
- በረዶ ለመሥራት
- ለቤት እንስሳት የመጠጥ ውሃ ለመስጠት
በፍጹም የውኃ ማጣሪያ ማሽኖችን ብቻ ተማምነው ውኃ ከማፍላት እንዳይዘናጉ።
ለዝርዝሩ የዲሲ ውሀና ፍሳሽን መግለጫ ይህን ተጭነው ያንብቡ::
—-
ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶች ካሏችሁ ራሳቸውን ከበሽታ እንዲጠብቁ ይህን መረጃ አጋሯቸው።