2

ዛሬ ሐሙስ ፌብሯሪ 13 የአሜሪካ ኢሚግሬሽንና ድንበር ጥበቃ ባወጣው መግለጫ ኤርትራዊውን ስደተኛ ዑቑበስላሴ ክፍለማርያም ዘርዬን በቁጥጥር ስር አውሎ ዲፖርት ሊያደርገው እንደሆነ አስታውቋል። ይህም በአደባባይ ስማቸው ከተጠቀሱ የዲፖርቴሽን ሰለባዎች የመጀመሪያው ኤርትራዊ ያደርገዋል።

ዑቑበስላሴ ለዚህ የበቃው በ2013 በአዛውንቶች መጦሪያ ቤት በሚሰራበት ወቅት በሁለት አዛውንቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመፈጸሙ ተጠርጥሮ ከታሰረ በኋላ ወንጀለኛ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ አይስ (ICE) አስታውቋል።

የፍርድ ቤት ክስ ዶሴዎች እንደሚያሳዩት ዑቑበስላሴ በ2013 ፍራንቼስካን ቪላ በሚባለውና በብሮክን አሮው ኦክላሆማ ባለ የአዛውንቶች መጦሪያ በሚሰራበት ወቅት የ80 እና የ93 ዓመት እድሜ ያላቸው አዛውንቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመፈጸሙ እንደሆነ ያሳያል። ዑቑበስላሴ ይህንንም ተግባር ሲፈጽም አብረውት የሚሰሩት በድንገት እንደደረሱበትና ሱሪውን እንደሰበሰበ የፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል ሲል በወቅቱ የወጡ ዜናዎች ጠቁመዋል።

ቀጣሪዎቹም ሴፕቴምበር 11 2013 ለፖሊስ ጉዳዩን ያሳወቁ ሲሆን በተደረገው ምርመራም ወንጀሉን መፈጸሙንና ከስድስት እስከ ሰባት ወር ለሚደርስ ጊዜም አዛውንቶቹ ላይ ጥቃቱን ሲያደርስ እንደቆየ ቃሉን ሰጥቶ አምኗል። ፖሊስ በወቅቱ እንዳሳወቀው ዑቑበስላሴ ባለ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንደሆነና በአካባቢው ለ2 አመት ሲሰራ እንደቆየ አሳውቀዋል።

በጃንዋሪ 2014 በሶስት መዝገቦች በአንደኛ ደረጃ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በያንዳንዱ መዝገብ አስር አስር አመት ተፈርዶበት ወህኒ ወርዶ ነበር።
በግንቦት 2022፤ ከተፈረደበት ከ8 ዓመት በኋላ የታሰርኩት ያላግባብ ነው፤ ወንጀሉን አልፈጸምኩም፤ ከተበዳዮቹጋ በፍቃዳቸው ነው ግንኙነት የፈጸምነው፤ የእምነት ቃሌን የሰጠሁት ተገድጄ ነው፤ ጠበቃዬም በአግባቡ አልተከራከረልኝም ብሎ ይግባኝ ቢጠይቅም በዩ ኤስ ዲስትሪክት ኮርት የሰሜናዊ ኦክላሆማ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት የይግባኝ መጠየቂያ ጊዜ አልፏል በሚል ይግባኙን ውድቅ አድርጎበታል።

በ ዑቑበስላሴና በሌላ ናይጄርያዊ ተመሳሳይ ወንጀል ምክንያት ኦክላሆማ በአዛውንቶች መጦሪያ የሚሰሩ ሰራተኞች የጣት አሻራ በመስጠት ከወንጀል ነጻ መሆናቸው ካልተረጋገጠ በስተቀር እንዳይቀጠሩ የሚል ህግም ከ2024 ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.