
ትላንት ፌብሯሪ 14 2025 የፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ ባወጣው መግለጫ ከአርብ ፌብሯሪ 14 2025 ጀምሮ ማንኛውም ለአቅመ አዳም ወይንም ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰ/ች ታዳጊዎች አርብና ቅዳሜ ብቻቸውን ከምሽት 5pm እስከ ንጋት 5am ድረስ ወደ ናሽናል ኃርበር ድርሽ እንዳይል ደንግገዋል። ይህ የሆነው ደሞ በርካታ ለአቅመ አዳምና ሄዋን ያልደረሱ ታዳጊዎች ያለ ወላጅ ቁጥጥር አካባቢው ላይ መበርከታቸውን ተከትሎ በአካባቢው ነዋሪዎችና ነጋዴዎች በቀረበ ጥያቄ እንደሆነ የካውንቲው ፖሊስ አስታውቋል።

ማንኛውም ከ18 ዓመት በታች የሆነ ሰው በተከለከሉ ሰዓታት ውስጥ ብቻውን ከተገኘ ወላጆች እስከ 250$ ቅጣት እንደሚቀጡ ተነግሯል።
ሆኖም ታዳጊዎች በነዚህ ሰዓታት ከወላጆቻቸውጋ ቢሆኑ፤ ወይም እድሜው ከ21 ዓመት በላይ ከሆነና የዋላጆቻቸው ፍቃድ ካለው ሰውጋ ቢገኙ፤ ከእምነት ተቋማት ሲመጡ ወይንም ወደ ዕምነት ተቋማት ሲሄዱ ቢገኙ፤ አልያም ከትምህርትና ከስራ ቤት ወደ ቤት ሲሄዱ ቢገኙ ወይንም በቤታቸው ፊለፊት ባለ መንገድ ላይ ሲጫወቱ ቢገኙ ይህ ህግ እንደማይመለከታቸው ተነግሯል።
