
በሜሪላንድ የመወሰኛ ምክር ቤት የሀዋርድ ካውንቲን በሚወክሉት ተወካይ ቨኔሳ አተርቤሪና (ዴሞክራት) የፍሬድሪክ ካውንቲ ተወካይ በሆኑት ክሪስ ፌይር (ዴሞክራት) አርቃቂነት በቀረበው በዚህ አዲስ ሜሪላንድ ትምህርት ከሪኩለም ማሻሻያ መሰረት የጤና ትምህርቶች በተለይም ከቤተሰብ ህይወትና ስርዓተ ጾታ (Human Sexuality)በተጨማሪ ጾታዊ ፍላጎትና ጾታዊ ማንነት፤ እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ የሶሻል ሚድያና ኢንተርኔት አጠቃቀም እንደ አንድ የትምህርት አይነት ሆነው ከፕሪ ኬ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲካተቱ በማሻሻያው ላይ ቀርቧል።

ከዚህ ቀደም የነበረው ፍሬም ወርክ በዋናነት 6 ዘንጎች የነበሩት ሲሆን እነሱም የሚከተሉት ናቸው።
- Mental and Emotional Health (አዕምሯዊና ስሜታዊ ጤና)
- Substance Abuse prevention (ከአደገኛ ሱሶች መከላከል)
- Family Life and human sexuality (የቤተሰብ ህይወትና ስርዓተ-ጾታ)
- Safety and Violence prevention (ደህንነትን መጠበቅና ረብሻን መከላከል)
- Healthy eating (ጤናማ አመጋገብ)
- Disease prevention and control (በሽታ መከላከልና መቆጣጠር)
አሁን በቀረበው ረቂቅ ማሻሻያ ደሞ ካሉት በተጨማሪ የሚከተሉት እንዲካተቱ የምክረ ኃሳብ ቀርቧል
- Health promotion
- Gender Identity and Sexual Orientation (ጾታዊ ፍላጎትና ጾታዊ ማንነት)
- Safe and appropriate social media and internet use (ደህንነቱ የተጠበቀ የሶሻል ሚድያና ኢንተርኔት አጠቃቀም)
ይህ ምክረ ኃሳብ ከሰሞኑ በሜሪላንድ መወሰኛ ምክር ቤት ቀርቦ ከተነበበና ማብራሪያ ከተሰጠበት በኋላ ወደሚመለከተው የምክር ቤቱ ኮሚቴ ተላልፏል። ሙሉውን ንባብና ጥያቄና መልስ ከቪዲዮው ማየት ይችላሉ። (ከደቂቃ 26፡30 ጀምሮ ይመልከቱ)
በዚህ ማሻሻያ ላይ የድጋፍና የተቃውሞ ድምጾች ከህዝብ የተጠየቁ ሲሆን በጠቅላላው 44 መስካሪዎች ይህን ማሻሻያ የተቃወሙ ሲሆን 18 መስካሪዎች ደሞ ድጋፋቸውን ሰተዋል። 5 መስካሪዎች ደሞ የተወሰነ ማሻሻያ ከተደረገበት በኋላ፤ በተለይም ወላጆች ልጆቻቸውን ከማይፈልጉት ትምህርት እንዲያስወጡ የሚፈቅዱ ቃላቶችና ሀረጎች አግላይ ስለሆኑ እንዲወገዱና ማንኛውም ወላጅ ቢፈልግም ባይፈልግም ልጆቹ እነዚህን ትምህርቶች እንዲማሩ የሚያስገድድ ህግ እንዲጨመርበት ጠይቀዋል።
ማሻሻያውን ከተቃወሙት መኃል የሀዋርድ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አንዱ ሲሆን ተቃውሟቸውን እንደሚከተለው አቅርበዋል።

የኢትዮጲክ ባልደረቦች ለአንባቢዎች የጠራ መረጃ ይዞ ለመምጣት በማሰብ እኚህን ተወካዮች ስለዚህ ማሻሻያ ቃለ መጠይቅ ሊያደርጉላቸው አስበዋል። እርስዎም የሜሪላንድ ነዋሪ ከሆኑና የዚህን ማሻሻያ ላይ ጥያቄ ካለዎት ከስር ባለው ፎርም ወይንም ይህን ተጭነው ጥያቄዎን ይላኩልንና እንጠይቅልዎታለን።