
ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ ከሰሞኑ እንዳስነበበው የአሜሪካ ድንበር ጠባቂዎች በ2025 ብቻ በአገሪቱ ደቡባዊ ድንበር በቴክሳስ በኩል የዶሮ እንቁላል በኮንትሮባንድ ይዘው ሊገቡ የሞከሩ 90 ሰዎችን መያዙንና በ16 የደንብ መተላለፍ ቅጣት በጠቅላላው አራት ሺህ ዶላር የሚገመት የቅጣት ትኬት እንደሰጠ አስታውቋል፡፡
ማንኛውንም ያልበሰለ እንቁላል፤ ያልበሰለ የዶሮ ስጋ እንዲሁም ማንኛውም የወፍ አይነት ይዞ ድንበር ማቋረጥ ወንጀል እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ተጓዦች ከነዚህ የተከለከሉ ነገሮች አንዱን እንኳ ከያዙ ለድንበር ተቆጣጣሪዎች እንዲያሳውቁ አለበለዚያ ግን ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተናግሯል፡፡
ከኦክቶበር 2024 እስከ ፌብሯሪ 2025 ድረስ ባለው ጊዜ በኮንትሮባንድ ገብቶ በመንግስት የተወረሰ እንቁላል በ29 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡