@ethiopique202 (4)

የዋሽንግተን ኤሪያ የባይስክሊስቶች ማህበር የአዋቂዎች የባይስክል ስልጠና ለዲሲና አካባቢው ነዋሪዎች አዘጋጅቷል።

የሞንጎምሪ ትራንስፖርት ዲፓርትመንት ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሚጀምረው የፀደይ ወቅት በካውንቲው ነዋሪ ለሆኑ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ አዋቂዎች የባይስክል መንዳት ስልጠና ስፖንሰር ማድረጉን አስታውቋል። ስልጠናውን የሚሰጠው በ1972 የተመሰረተው የዋሽንግተን ኤሪያ የባይስክሊስቶች ማህበር ሲሆን እርስዎም በዚህ የፀደይ ወቅት የአንድ ተጨማሪ ክህሎት ባለቤት መሆን ከፈለጉ ይህን ሊንክ ተጭነው መመዝገብ ይችላሉ።

በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን ነዋሪውች አስቀድመው መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። የሞንጎምሪ ካውንቲ በከፊል ስፖንሰር ባደረገው በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ ተማሪዎች 10$ መክፈል ይጠበቅባቸዋል። በስልጠናው ወቅት ለተማሪዎች ብስክሌትና ሄልሜት ተዘጋጅቷል። ተማሪዎች ከፈለጉ የራሳቸውን ብስክሌትና ሄልሜት ይዘው መሄድም ይችላሉ።

ተማሪዎች በዚህ ስልጠና ያገኟቸዋል የተባሉት ክህሎቶች ብስክሌትን እንዴት ባላንስ እንደሚያደርጉ፤ እንዴት ማስነሳትና ማቆም እንደሚቻል፤ ፔድል እንዴት እንደሚመታና የመሳሰሉ መሰረታዊ ትምህርቶችን ይማራሉ ተብሏል።

የሞንጎምሪ ካውንቲ ያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች የሚከተሉት ሲሆኑ በአቅራቢያዎ ባለ ቦታ በመሄድ ተመዝግበው በመማር የዚህ ክህሎት ባለቤት መሆን ይችላሉ።

Adult Basic Skills Bike Class schedule:  

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.