
የአሌክሳንድርያ ከተማ ለማርች ወር 2025 ክፍት የሆኑና ለከተማው አቅምን ያገናዘቡ የተባሉ የኪራይ ቤቶችን ዝርዝር ትላንት ማርች 4 2025 ላይ ለህዝብ ይፋ አድርጓል። በዚህ ዝርዝር ላይ በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች የሚገኙ ከስቱዲዮ ጀምሮ ባለ አንድ፤ ባለ ሁለትና ባለ ሶስት መኝታ መኖሪያ ቤቶች ዝርዝር የተካተቱ ሲሆን እድሚያቸው ከ62 በላይ ለሆኑ አዛውንቶችን ጨምሮ ለማንኛውም ሰው የሚሆኑ ቤቶች እንዳሉ ተጠቁሟል።
Advertisement

ገቢን ያገናዘቡ (አፎርደብል ቤቶችን) ለመከራየት ከዚህ ቀደም የነበረው የገቢ መጠን ከጃንዋሪ 2025 ጀምሮ የተስተካከለ ሲሆን አዲሱ የገቢ መጠን እንደሚከተለው ሰንጠረዥ እንደሚሆንም መረጃው ያመለክታል።

የነዚህን ቤቶች ሙሉ ዝርዝር ለማየትና ለማመልከት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ።