@ethiopique202 (5)


በጠቅላላው የአፎረደብል ሀውሲንግ ተጠቃሚ ለመሆን ሶስት አይነት መንገዶች አሉ። አንደኛው በከተማው አፎረደብል ሀውሲንግ ለማቅረብ በተቋቋመ ድርጅት አስተዳዳሪነት የሚከራዩ ቤቶች ላይ በተጠባባቂነት ተመዝግቦ ተራዎች ሲደርስዎት ባለቤት መሆን ነው። ሁለተኛው ደሞ የዲሲ መንግስት በየጊዜው በሚያወጣው የአፎርደብል ቤት ምዝገባ ላይ በተጠባባቂነት በመመዝገብ ተራዎ ሲደርስዎ የቤት መከራያ ቫውቸር ባለቤት በመሆን በፈለጉት ቦታ ያለ ቤት መከራይት ሁለተኛው መንገድ ነው።

ሶስተኛው ደሞ የዲሲ መንግስት ራሱ በሚያስተዳድራቸው ቤቶች ውስጥ ነው።

በዋሽንግተን ዲሲ ከላይ በተጠቀሰው የመጀመሪያው መንገድ የአፎርደብል ቤት ለማግኘት በዋናነት የተከራዮችን ምዝገባና ቅበላ የሚያደርጉት በከተማዋ የአፎርደብል ቤቶች በማከራየት የሚተዳደሩ የተለያዩ ባለቤቶች ናቸው።
እነዚህ አከራዮች ብዙውን ጊዜ ምዝገባ ሲጀምሩ ወይንም አፓርታማቸው ላይ የሚከራይ ቤት ሲኖር እዛው አፓርታማው ውስጥ ባሉ የማስታወቂያ ቦርዶችና የአፓርታማው መግቢያ ላይ ብቻ ነው የሚለጥፉት። አልፎ አልፎ የኢትዮጲክ አንባቢዎች የሚልኩልንን የክፍት ቤት መረጃዎች እዚሁ ስናጋራ ቆይተናል። ተመዝግበው ቤት የደረሳቸውም ምስጋናቸውን ሲቸሩን ቆይተዋል።

ይህም ሆኖ በምዝገባው ቀን በርካታ ሰዎች ከለሊት ጀምሮ ተሰልፈው በመጠበቅ ይመዘገባሉ።
የዲሲ መንግስት ይህንን ፍላጎት ለማሟላትና በተለይም ተከራዮች በቤት ፍለጋ እንዳይቸገሩ በማሰብ የሚከራዩ አፎርደብል ቤቶችን የሚፈልጉበት ድረ-ገጽ አዘጋጅቷል።
እርስዎም በዲሲ ያሉ አፎርደብል ቤቶችን ለማየት፤ ክፍት ቤት ያላቸውን ለመጠየቅ ከፈለጉ ይህንን ሊንክ በመጫን የአከራዮችን ሙሉ ዝርዝር ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉት በሙሉ የሴክሽን 8 አከራዮች ላይሆኑ ስለሚችሉ ከመወሰናችሁ በፊት በትክክል የአፎርደብል ቤት አከራይ መሆናቸውን፤ እንዲሁም የምን አይነት አፎርደብል ቤት አከራይ እንደሆኑ ማጣራት እንዳትረሱ። በተጨማሪም በከተማዋ ነዋሪ የሆኑና የቤት አልባነት አደጋ የተጋረጠባሸው ሰዎች ደሞ የዲሲ መንግስት ባዘጋጀው ድረገጽ ላይ በመግባት መረጃ ማግኘት ይችላል። በአከራዮቻቸው የመባረስ አደጋ የተጋረጠባቸው ሰዎች ደሞ ከዚህ ቀደም ኢትዮጲክ ከ51st ጋ በመተባበር ያዘጋጀችውን ዘገባ መመልከት ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ የዲሲ ቤቶች ልማት በስልክ ቁጥር (202) 671-4200 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.