@ethiopique202 (6)-1


በሲቲ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ኒው ዮርክ የክሬይግ ኒውማርክ የጋዜጠኞች ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት (Newmark Graduate School of Journalism at CUN) ለመጀመሪያ ጊዜ በጀመረውና በንድፈ ሀሳብና በተግባር ለሚሰጠው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትምህርት ለመሳተፍ ከተወዳደሩ በርካታ ጋዜጠኞች መሀከል ተወዳድረው ካሸነፉት መካከል አንዱ የኢትዮጲክ መስራችና አዘጋጅ ሔኖክ ይገኝበታል።

ይህ መልካም ዕድል እስካሁን ኢትዮጲክ በዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በአማርኛ ለማህበረሰቡ ስታቀርበው የነበረውን አገልግሎት በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የበለጠ አጠናክራ እንድትቀጥል እንደሚያደርጋት ይታመናል።

ይህ መልካም እድል እንዲገኝ ያደረጉትን የዘወትር አንባቢዎቻችንን፤ በየጊዜው መረጃ የምትልኩልንን፤ ስንሳሳት የምታርሙንንና አይዟችሁ በርቱ የምትሉንን እናንተኑ ለማመስገን እንወዳለን። በዚህ ዕድል ያገኘነው ዕውቀት እውነትም እንደተባለው ማህበረሰባችንን የምንጠቅምበት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.