@ethiopique202 (7)

ዋሽንግተን ዲሲ በታሪኳ በሙሉ የምትታወቀው በተራማጅ ፖሊሲዎቿና በተለይም ሁሉን አቃፊ በመሆኗ ነበር። ከሰሞኑ ታዲያ በፕሬዘደንት ትራምፕና በካቢኒያቸው አስተዳዳሪዎች በተደጋጋሚ በደረሰባቸው ተፅዕኖ ምክንያት የዲሲ ከንቲባ በርካት ተራማጅ ፖሊሲዎቻቸውን ሲያጥፉና ሲሽሩ ተስተውለዋል።


በስደተኞች ላይ ያለው ተጽዕኖ

ከሰሞኑ የቨርጂንያ ገቨርነር ግሌን ያንግኪን ባወጡት ትዕዛዝ የቨርጂንያ ስቴት ፖሊስና የማረሚያ ቤት ተቆጣጣሪዎች ከፌደራል ስደተኛ ቁጥጥር መስሪያ ቤትጋ ተባብረው እንዲሰሩ አልፎ ተርፎም አንዳንዶቹ ራሳቸው እንደ የስደተኛ ጉዳዮች ተቆጣጣሪ ሆነው እንዲያገለግሉ የሚያስችላቸውን ትዕዛዝ አዘዋል።ይህም ፖሊሶች ስደተኛ ነው ብለው የጠረጠሩትን ሰው በመንገድ አስቁመው መታወቂያውን ወይንም መንጃ ፍቃዱን እንዲጠይቁ ያስችላቸዋል። ይህን ተከትሎም የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘርም በተመሳሳይ የዲሲን ፖሊስ የስደተኛ ጉዳዮች ቁጥጥር ላይ እንዲሳተፍ ያዙ ይሆን? የሚል ጥያቄ ያጭራል።


ከንቲባዋ በዲሴምበር 2024 እንደተናገሩት የዲሲ ፖሊስ የስደተኛ ጉዳዮችን እንደማይቆጣጠር አስታውቀው ነበር።ሆኖም ከሰሞኑ ከፌደራል መንግስቱ በተደረገባቸው ጫና በርካታ ከዚህ ቀደም ያደርጓቸዋል ተብሎ የማይጠበቁ ውሳኔዎችንና ድርጊቶችን ሲያደርጉ ተስተውለዋል።


ለምሳሌም ታሪካዊውና የዚህ ዘመን የትግል ምልክት የሆነው በዲሲ ዳውንታውን ሲክስቲንዝ ስትሪት ላይ የሚገኘውን የብላክ ላይቭስ ማተር ፕላዛ ካላነሱ የፌደራል የገንዘብ ድጋፍ ይቆማል በሚል የሪፐብሊካን ኮንግረስ አባላት ማስፈራራታቸውን ተከትሎ 48 ባልሞላ ጊዜ ከንቲባዋ ትዕዛዙን እንደሚተገብሩ አስታውቀው ወደ ስራ ገብተዋል።


ምንም እንኳ አንዳንድ የዲሲ ካውንስል አባላት የከንቲባዋን እርምጃና ታዛዥነት ቢቃወሙትም ከንቲባዋ የፌደራል መንግስትን ፍላጎት ከማሳካት ወደኋላ አላሉም።

በተመሳሳይ ፕሬዘደንት ትራምፕ ከሰሞኑ ከንቲባዋ በከተማዋ የሚገኙ ቤት አልባዎችን (የጎዳና ተዳዳሪዎችን) ካላባረሩ ድንኳኖቻቸውንም ካላጸዱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ካሳወቁ በሁዋላ ከንቲባዋ የዲሲን የራሱን የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ ህግ በመጣስ ቤት አልባዎችን በ24 ሰዓት ማስጠንቀቂያ አፈናቅለዋል።


የስደተኞች ጉዳይን በሚመለከትም የዲሲ ከንቲባ ከዚህ ቀደም በኩራት ዋሽንግተን ዲሲ ስደተኞችን በዕቅፍ ተቀብላ የምታስተናግድ ከተማ እንደሆነች ተናግረዋል። ሆኖም ከሰሞኑ በርካታ ለስደተኞች በተለይ ደሞ ለወንጀለኛ ስደተኞች ጭምር ጥላ ከለላ ሆነዋል ተብለው የተወቀሱ ከንቲባዎች በኮንግረስ ቀርበው ምስክረነት መስጠታቸውን ተከትሎ የዲሲ ክንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ዲሲ ለስደተኞች የምትሰጠውን ድጋፍና ከለላ በሚመለከት የሚያስረዳውንና በተለይም በስደተኞች ተዘውትረው ለሚጠየቁ ጥያቄዎች መልስ በማቅረብ ያገለግል የነበረውን ድረ-ገጽ ዘግተዋል።

ይህንን ተከትሎም በከተማዋ እንደ ትልቅ ቅርስ ይቆጠር ለነበረው ለብላክ ላይቭስ ማተር ፕላዛና ለቤት አልባ ነዋሪዎቿ ያልተመለሰች ዲሲ ለስደተኞች ትመለስ ይሆን ወይ የሚል ስጋትና ጥያቄ ያጭራል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.