@ethiopique202-1

በ2024 ጽድቆ ወደስራ የተገባበት የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በጀት በኮንግረስ ሪፐብሊካን መሪዎች ረቂቅ በጀት መሰረት የ1.1 ቢልየን ዶላር ቅናሽ እንዲኖረው ተጠይቋል፡፡ ይህም በተለይ አብዛኛው የከተማው በጀት በሰራተኛ ቅጥር ወጪ ለሚሆንባት የዲሲ ከተማ ከፍተኛ መናጋትን እንደሚያስከትልና በፌደራል መንግስት ተቀናሽ የተደረጉ ሰራተኞች መፍትሄ ባላገኙበት ሁኔታ የከተማው መንግስት ሰራተኞችም በተመሳሳይ ከስራ መቀነስ እንደሚያጋጥማቸው ተሰግቷል፡፡ 

የመወሰኛ ምክር ቤት የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካዮች ቅዳሜ ይፋ ያደረጉትና እስከ ሴፕቴምበር 30 2025 የፌደራል መንግስትን ከመዘጋት ያድናል የተባለለት በጀት የዲሲ መንግስት ያጸደቀውን የ2025 በጀት ወደጎን ትቶ ዲሲ በ2024 በነበረው በጀት እንዲተዳደር የሚጠይቅ ሲሆን ይህም የከተማዋን በጀት በ1።1 ቢልየን ዶላር እንዲቀንስ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የዲሲ መንግስትም ይህ በጀት ከጸደቀ በርካታ ሰራተኞቹ እንደሚቀነሱ እንዲሁም በርካታ አገልግሎቶች እንደሚቋረጡ አስታውቋል፡፡ 

የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር በጉዳዩ ላይ ሲናገሩ “የፌደራል መንግስት ዋሽንግተን ዲሲን ልክ እንደ አንድ የፌደራል መስሪያ ቤት ነው እያየው ያለው፡፡ ማሳወቅ የምንፈልገው ነገር እኛ የፌደራል መንግስት መስሪያቤት አይደለንም፡፡” ብለዋል፡፡ ከንቲባዋ አክለውም የ2024 በጀት ሪፖርታቸው በአግባቡ ያለምንም ግድፈት ኦዲት እንደተደረገና ይህንን የሚያስወስናቸው ምንም ምክኛት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

የዲሲ ካውንስል አባል ፊል ሜንደልሰንም እንዲህ ብለዋል፡፡ “የሚቀነሰው በጀት ገንዘቡ የተገኘው ብዋሽንግተን ዲሲ ከሚሰበሰብ ግብርና ሌሎች ገቢዎች በመሆኑ የፌደራል መንግስቱ ይህን ማድረግ የለበትም፡፡ ብዙ ሰዎች የዲሲ መንግስት በፌደራል መንግስት ድጎማ የሚኖር ይመስላቸዋል እውነታው ግን ያ አደለም፡፡ ከተማው የሜተዳደረ በራሱ ገቢ ነው፡፡” 

ይህን የሪፐብሊካኖች ውሳኔ ተከትሎ በርካታ የዲሲ ፖለቲከኞችና ተወካዮች ትላንት በካፒቶል ተገኝተው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ 

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.