@ethiopique202 (32)

የላውደን ካውንቲ ሸሪፍ ቢሮ በሰሜናዊ ቨርጂንያ የመጀመሪያው የሆነውን በማረሚያ ቤቱ ያሉ የኢሚግሬሽን እስር ተዕዛዝ የተላለፈባቸውን ስደተኞችን ለፌደራል ኢሚግሬሽን አሳልፎ ለመስጠት ማርች 27 ላይ በፊርማ እንደተስማማ ተነግሯል።

ይህን ተከትሎም የካውንቲው ማህበረሰብ አካላት ባሳለፍነው ሐሙስ ኤፕሪል 3 በላውደን ካውንቲ ሸሪፍ ቢሮ ፊትለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅተው ነበር።


የተቃውሞው አስተባባሪ ከሆኑት አንዱ ዊል ስቴዋርት እንዳሉትም ወንጀል የሌለበአቸው ሰዎች ከወንጀለኞችጋ አስፈላጊውን የህግ ሂደት ሳያልፉ ዲፖርት መደረጋቸውን እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል።


አንድ ሰው ቪዛው ካልተቃጠለ ወይንም የመኖሪያ ፍቃድ ካለው ያ ሊከበርለት እንደሚገባና ካልሆነ እንኳ በአግባቡ በፍርድ ቤት እስኪወሰንበት ወደ ዲፖርቴሽን እንዳያመራ መደረግ አለበት ብለዋል።\


ሌላኛው ሰልፈኛና የላውደን ካውንቲ ዲሞክራቲክ ኮሚሽን ሊቀመንበር ዴቪድ ባወር ደሞ “ላውደን ካውንቲ ማንኛውም ሰው፤ ምንም አይነት ስደተኛ ቢሆን በነጻነትና በደህንነት ሊኖር የሚገባው ቦታ መሆን አለበት” ሲሉ ተደምጠዋል። ከስር ያለውን መግለጫም በዴሞክራቲክ ፓርቲ ስም አውጥተዋል።


የፖሊስ ቃል አቀባይ የሆኑት ቶማስ ጁሊያ በበኩላቸው ይህ አሰራር አዲስ እንዳልሆነና ከዚህ ቀደምም ሲሰራበት የቆየ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ ትብብር የሚመለከተው ባጠፉት ጥፋት ወይንም ወንጀል የተፈረደባቸው እስረኞችን ብቻ እንደሆነም አክለው ተናግረዋል።


የአሁኑን የተለየ የሚያደርገው ከዚህ ቀደም እስረኛ ከመለቀቁ በፊት ለሌሎች ኤጀንሲዎች ያንን እስረኛ በሌላ ወንጀል ይፈልጉት እንደሆነ ይጠየቃል ከዛ ያ ቀን ሳያልፍ በፊት ከመጡ ይወስዱታል አልያ ግን ይለቀቃል።
በአሁኑ ስምምነት ግን ለአንድ ቀን ብቻ የነበረው ጥበቃ ወደ ሁለት ቀን ያድጋል። ይህም ለ አይስ (ICE) ፖሊሶች በቂ ጊዜ ይሰጣቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በዚህ በአዲሱ ስምምነት መሰረት ከ10 እስከ 20 የሚደረሱና በማረሚያ ቤት የተመደቡ ፖሊሶች በአይስ ፕሮቶኮል ስልጠና እንዲወስዱ እንደሚደረግ ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪ ግን የካውንቲው የሸሪፍ ቢሮ ስደተኞችን የማፈስ፤ ወይንም የማሰር ስራዎች ላይ እንደማይሰማራ ጠቁመዋል።


እንደ ቃል አቀባዩ ከሆነ አይስ ከጃንዋሪ 1 ጀምሮ እስከ ማርች 31 80 የማሰሪያ ወረቀቶችን የላከ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 42 ያህሉን ወስዷቸዋል።

የስምምነቱ ትልቁ አላማው ለአይስ ፖሊሶች ተጨማሪ ጊዜ መስጠት እንጂ የላውደን ፖሊሶች ወርደው ስደተኞችን ወደማፈስና ማሰር እንደማይሰማሩ መታወቅ አለበት ብለዋል። ይህ የፌደራል መንግስት ስራ ነው ሲሉም አክለዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.