
የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ዛሬ ማክሰኞ ኤፕሪል 8 ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ የ32 ዓመት ወጣት የሆነችውን ሄለን ዴቪስን ወይንም ሄለን ወሰኑን አፋልጉኝ ብሏል፡፡
ፖሊስ በመግለጫው እንዳስቀመጠው ሄለን ቁመቷ 5 ጫማ ከ3 ኢንች ስትሆን 125 ፓውንድ ትመዝናለችም ብሏል፡፡ ሄለን ቡናማ አይኖችና ጥቁር ጸጉር እንዳላትም ተነግሯል፡፡
ሄለን አርብ ማርች 21 ምሽት በፌንተን ስትሪት ከሚገኘው ቤቷ እንደወጣች አልተመለሰችም፡፡ በወቅቱ ምን አይነት ልብስ ለብሳ እንደነበር አልታወቀም፡፡
ማንኛውም መረጃው ያለው ሰው በስልክ ቁጥር 301-279-8000 በመደወል መጠቆም ይችላል ተብሏል፡፡