@ethiopique202-1

የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ዛሬ ረቡዕ ኤፕሪል 9 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ የአሜሪካ የስደተኞች ቢሮ (USCIS) በቢሮው ጉዳያችው እየታየላቸው ያሉ ስደተኞችን የማህበራዊ ሚድያ አካውንቶች እንደሚበረብርና ጸረ እስራኤል አቋም የሚያንጸባርቁ ወይንም በአካል በአይሁዳውያን ግለሰቦች ላይ ጥቃት ያደረሱ ሰዎችን ማመልከቻ እንደማይቀበል አስታውቋል፡፡

ይህ ውሳኔ የግሪን ካርድ ለማግኘት ለሚያመለክቱ ሰዎች፤ በአሜሪካ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ የሌላ አገር ዜጋ ተማሪዎችና በትምህርት ተቋማት በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ምሁራንን እንደሚመለከት በመግለጫው ተነግሯል፡፡

ይህ ውሳኔ ፕሬዘደንት ትራምፕ ካወጡት ኤክሲኩቲቭ ኦርደርጋ ተያያዥ በሆነ መልኩ እንደሚተገበርና በተለይም ጸረ እስራኤል በሆነ የሽብር ተግባራትን የሚደግፉ፤ ወይንም እንደ ሀማስ፤ የፍልስጤም እስላማዊ ጂኃድ፤ ሄዝቦላ፤ ወይንም  ሁውቲዎችን (አንሳር አላህ) የመሳሰሉ ጸረ እስራኤል የሆኑ ድርጅቶችን የሚደግፉ ሰዎችን ከማንኛውም የኢሚግሬሽን ጉዳይ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ እንደሚያግድ አስታውቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት የህዝብ ግንኙነት የሆኑት ትሪሻ ማክላውሊን “በዩናይትድ ስቴትስ የሌሎች አገር ዜጎችን የሽብር ተቋማት ደጋፊዎችን እንዲመጡ ለመፍቀድም ሆነ እዚህ ሆነው ያንን ባህርይ የሚያንጸባርቁ ሰዎችን እንዲቆዩ የምንፈቅድበት ምክንያት የለም፡፡” ብለዋል፡፡ ኃላፊዋ አክለውም “ሴክረተሪ ኖኤም በግልጽ እንዳስቀመጡት ሰዎች ኃሳብን በነጻ መግለፅ በሚል የህገ መንግስት ሽፋን ጸረ እስራኤል አቋማቸውን ማንጸባረቅ እንደማይችሉና ይህን የሚያደርጉ ሰዎች በፍጹም እዚህ አገር መምጣትም መኖርም እንደማይችሉ ሊያውቁ ይገባል” ብለዋል፡፡

በዚህ መመሪያ መሰረትም የአሜሪካ ስደተኞች ቢሮ (USCIS) የአመልካቾች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰዎች ጸረ እስራኤል የሆኑ ሀሳቦችን ወይንም ተቋማትን ከደገፉ፤ ካንጸባረቁ፤ ካጋሩ፤ በኢንተርቪው ቀናቸው ላይ እንደ አሉታዊ ተግባር ተደርጎ እንደሚቆጠርና ይህም ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡ 

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.