የዋሽንግተን ዲሲ ጤና ቢሮ ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ ኤፕሪል 5 ቀን ከሰዓት ከ3፡30 pm እስከ 6፡30 pm...
Month: April 2025
ዛሬ ሰኞ ኤፕሪል 14 በዋይት ሀውስ ኦፊሴላዊ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የኤል ሳልቫዶር ፕሬዘደንት የሆኑት ናይብ ቡኬሌ በስህተት ከፕሪንስ ጆርጅ...
የሜትሮፖሊታን አካባቢ ሬስቶራንት አሶሴሽን በሰዋና ከ200 በላይ የሬስቶራንት ባለቤቶች ተሳትፈውበታል በተባለበት ጥናት 47% የሚሆኑት በ2024 የደንበኞቻቸው ቁጥር እንደቀነሰ ያስታወቁ...
የፌደራል አስቸኳይ ይግባኝ ለመስማት ከሰሞኑ ቀጠሮ ይዞ የነበረው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መንግስት በስህተት ዲፖርት ያደረገውን ሰው እንዲመልስ ውሳኔውን...
ቻይና ከነገ ሀሙስ ጀምሮ በአሜሪካ ምርቶች ላይ 84 ከመቶ ታሪፍ መጣሏን በማስታወቋ፤ ከአሜሪካ ጋር በተባባሰ የንግድ ጦርነት ውስጥ የገባች ሲሆን፤ ”እስከ መጨረሻው ለመታገል” ቃል መግባቷን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል ። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ አጠቃላይ ታሪፉን ወደ 104 በመቶ ከፍ ካደረጉ በኋላ ቤጂንግ በርካታ የመከላከያ እርምጃዎችን ወስዳለች። ቤጂንግ በዓለም ንግድ ድርጅት ውስጥ በአሜሪካ ላይ ተጨማሪ አዲስ ክስ እየመሰረተች ያስታወቀች ሲሆን፤ በተጨማሪም ከቻይና ኩባንያዎች ጋር የንግድ ልውውጥ ባላቸው የአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ ተጨማሪ ገደቦችን እንዳስቀመጠች አስታውቃለች። ይሁን እንጂ ቻይና ሌሎች የዓለም መንግስታት እያደረጉ እንዳሉት ከዋይት ኃውስ ጋር እየተደራደረች እንደሆነ ከማስታወቅ ተቆጥባለች። ቻይና ባለፈው ሳምንት አርብ ነበር አሜሪካ ለጣለችባት ታሪፍ ተመጣጣኝ ነው ያላቸውን 34 ከመቶ ታሪፍ መጣሏን ያስታወቀችው። ይህን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቻይና ላይ የተጣለውን ታሪፍ ወደ 50 ከመቶ ያሳደጉት ሲሆን ከቻይና ጋር ድርድር አያስፈልግም በማለት ድርድሩን አቋርጠዋል። እስካሁን ድረስ ባለው የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን እረቡ ዕለት እንዳሉት “ዩናይትድ ስቴትስ ጉዳዮችን በውይይት እና በድርድር ለመፍታት በእውነት ከፈለገች የእኩልነት፣ የመከባበር እና የጋራ ተጠቃሚነትን አስተሳሰብ ማዳበር አለባት” በማለት ለድርድር እምብዛም ፍላጎት እንደሌላት ጠቁመዋል። ይህንን እሰጥ አገባ ተከትሎም ፕሬዘደንት ትራምፕ በቻይና ላይ የጣሉትን የታሪፍ መጠን ወደ 125%...
በቨርጂኒያ ግዛት የፍሬድሪክስበርግ ባለሥልጣናት ትላንት ማክሰኞ እንዳስታወቁት፤ ስፖጽልቬንያ ካውንቲ ፍሬድሪክ ከተማ በተፈጸመ ተኩስ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ በትንሹ ሌሎች ሦስት ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸው “ሁሉም ተጠርጣሪዎች” በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አስታውቀዋል። ሁለት የ16 ዓመት ታዳጊዎች፣ አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ እና ጀርማያ አፕሰን የተሰኘ የ18 ዓመት ወጣት በቁጥጥር ስር ውለው “ተደራጅተው መሳሪያ በመጠቀም ከባድ ጉዳት በማድረስ እና ህገወጥ ድርጊት በመፈጸም” በሚል መከሰሳቸውን ፖሊስ ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ባሰራጨው መረጃ አመልክቷል። ይህ የወንጀል ተግባር ትላንት አመሻሽ 5:30 አካባቢ መፈጸሙን ፖሊስ መረጃው እንደደረሰው አስታዉቋል። በቦታው ከነበሩትና አደጋው ከደረሰባቸው ስድስት ሰዎች መካከል ሦስቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ብለዋል ። በጥቃቱ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም በሰዓቱ ተገልጿል። አደጋው የደረሰው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ...
በቨርጂኒያ ግዛት ፍሬድሪክስበርግ የሊ ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሥስተኛ ክፍል ተማሪ መማሪያ ክፍል ውስጥ መሳሪያ ማምጣቱን ተክትሎ፤ ወላጆቹ በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸው የስፖትስልቫኒያ የፖሊስ ጽህፈት ቤት ገልጿል። ታዳጊው የጠዋት ስናክ ለመብላት እጁን ቦርሳ ውስጥ ከቶ በሚፈልግበት ሰዓት መሳሪያው መባረቁን ፖሊስ አስታውቋል። የፖሊስ ሃላፊ ሜጀር ኤሊዛቤት ስካት “መሳሪያ ታጣቂዎች እንዲህ ዓይነት ክስተት እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው” በማለት አሳስበዋል። ፖሊስ ሰኞ ዕለት ከጠዋቱ 11 ሰዓት በፊት በተፈጠረው ክስተት ማንም አለመጎዳቱን ገልጾ፤ ስፍራውን እየተጠበቀ ተማሪዎች ክፍሉን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል። የታዳጊው ሁለቱም ወላጆቹ የአምስት ሺህ ዶላር ቦንድ እንዲከፍሉና የፊታችን አርብ በስፖትስላቬኒያ ካውንቲ የታዳጊዎች እና የቤት ውስጥ ጉዳይ ፍ/ቤት እንዲገኙ ታዘዋል። የተማሪው መምህር ማንነታቸው ባይገለጽም በፍጥነት ተማሪዎቹን በማሰባሰብ እና ደህንነታቸውን በመጠበቅ ለወሰዱት እርምጃ ሙገሳ ተችሯቸዋል። ፖሊስ አስፈላጊው የምክር እና የማረጋጋት አገልግሎት ለሊ ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መምህራን እና ወላጆች እየተሰጠ መሆኑም ገልጿል
በሜሪላንድ ግዛት ውስጥ የሞንጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ በኢሚግሬሽን አስገዳጅ አፈጻጸም ስራዎች ውስጥ በመግባት ህገወጥ ስደተኞችን ማሰስ እና ማሰር ውስጥ እንደማይሳተፍ የካውንቲው የሥስተኛ እዝ አዛዥ የሆኑት ጄሰን ኮኪኖስ በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ኮኪኖስ አቋማችን አይለወጥም ብለዋል። በተመሳሳይ የሞንጎመሪ ካውንቲ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ኬት ስቱዋርት የኮኪኖስ አቋም ደግፈው ያንጸባረቁ ሲሆን፤ በዚሁ ሳምንታዊ አጭር መግለጫ ላይ፣ ማንኛውም ሰው – ምንም ዓይነት የኢሚግሬሽን ሁኔታ ላይ ቢሆንም ሊያሳበው የሚገባው የህዝብ ደህንነት ስጋት ብቻ መሆኑን በመግለጽ ነዋሪዎች ሳይፈሩ የሚጋጥሟቸውን የህግ ጥሰቶች በአግባቡ እንዲያመለክቱ አሳስበዋል። ኮኪኖስ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ በቅርቡ በሎንግ ብራንች፣ ብዙ ስደተኞች ባሉበት ሰፈር ውስጥ በተደረገ የማኅበረሰብ ስብሰባ ላይ ተሳትፈው እንደነበር በመግለጽ ሰዎች ያለፍርሃት ከፖሊሶች ጋር ስላለባቸው ስጋት ሲነጋገሩ ማየታቸው እና ያለው መቀራረብ እንዳሰደነቃቸው ገልጸዋል። የሞንጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት የዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ አስፈጻሚ አይስ የአካባቢ ህግ አስከባሪ መኮንኖችን እንዲጠቀም የሚፈቅደውን የኢሚግሬሽን ስምምነት 287(g) ውስጥ ተሳታፊ አይደለም። የካውንቲው ፖሊስ ሦስተኛ እዝ ክፍል ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ዋይት ኦክ እና በርተንስቪልን አካባቢዎችን የሚያጠቃልል ነው። በተያያዘ የቨርጂንያ ገቨርነር የስቴት ፖሊሶች እንዲተባበሩ...
የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ዛሬ ረቡዕ ኤፕሪል 9 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ የአሜሪካ የስደተኞች ቢሮ (USCIS)...
የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ዛሬ ማክሰኞ ኤፕሪል 8 ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ የ32 ዓመት ወጣት የሆነችውን ሄለን ዴቪስን ወይንም ሄለን ወሰኑን...