በሜሪላንድ ግዛት ውስጥ የሞንጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ በኢሚግሬሽን አስገዳጅ አፈጻጸም ስራዎች ውስጥ በመግባት ህገወጥ ስደተኞችን ማሰስ እና ማሰር ውስጥ እንደማይሳተፍ የካውንቲው የሥስተኛ እዝ አዛዥ የሆኑት ጄሰን ኮኪኖስ በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ኮኪኖስ አቋማችን አይለወጥም ብለዋል። በተመሳሳይ የሞንጎመሪ ካውንቲ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ኬት ስቱዋርት የኮኪኖስ አቋም ደግፈው ያንጸባረቁ ሲሆን፤ በዚሁ ሳምንታዊ አጭር መግለጫ ላይ፣ ማንኛውም ሰው – ምንም ዓይነት የኢሚግሬሽን ሁኔታ ላይ ቢሆንም ሊያሳበው የሚገባው የህዝብ ደህንነት ስጋት ብቻ መሆኑን በመግለጽ ነዋሪዎች ሳይፈሩ የሚጋጥሟቸውን የህግ ጥሰቶች በአግባቡ እንዲያመለክቱ አሳስበዋል። ኮኪኖስ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ በቅርቡ በሎንግ ብራንች፣ ብዙ ስደተኞች ባሉበት ሰፈር ውስጥ በተደረገ የማኅበረሰብ ስብሰባ ላይ ተሳትፈው እንደነበር በመግለጽ ሰዎች ያለፍርሃት ከፖሊሶች ጋር ስላለባቸው ስጋት ሲነጋገሩ ማየታቸው እና ያለው መቀራረብ እንዳሰደነቃቸው ገልጸዋል። የሞንጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት የዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ አስፈጻሚ አይስ የአካባቢ ህግ አስከባሪ መኮንኖችን እንዲጠቀም የሚፈቅደውን የኢሚግሬሽን ስምምነት 287(g) ውስጥ ተሳታፊ አይደለም። የካውንቲው ፖሊስ ሦስተኛ እዝ ክፍል ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ዋይት ኦክ እና በርተንስቪልን አካባቢዎችን የሚያጠቃልል ነው። በተያያዘ የቨርጂንያ ገቨርነር የስቴት ፖሊሶች እንዲተባበሩ...
ፌደራል
የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ዛሬ ረቡዕ ኤፕሪል 9 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ የአሜሪካ የስደተኞች ቢሮ (USCIS)...
የላውደን ካውንቲ ሸሪፍ ቢሮ በሰሜናዊ ቨርጂንያ የመጀመሪያው የሆነውን በማረሚያ ቤቱ ያሉ የኢሚግሬሽን እስር ተዕዛዝ የተላለፈባቸውን ስደተኞችን ለፌደራል ኢሚግሬሽን አሳልፎ...
አይስ (ICE) ወደ ኤልሳልቫዶር ዲፖርት ያደረገው የቬንዙዌላ ዜጋ ስደተኛ በስህተት እንደሆነና በአስተዳደራዊ ግድፈት ምክንያት ይህ ሊፈጠር እንደቻለ አስታውቆ ነበር።...
ዜናው የቢቢሲ ነው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ደቡብ ሱዳን ከአሜሪካ የተባረሩ ዜጎቿን ለመቀበል ዳተኛ በመሆኗ ምክንያት የደቡብ...
“እጃችሁን አንሱ” (Hands Off!) በሚል መርህ ቃል በመላው ዩናይትድ ስቴትስና በሌሎችም አገራት የፕሬዘደንት ትራምፕ አስተዳደርን የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ ለኤፕሪል...
ፕሬዘደንት ትራምፕ ዛሬ በዋይት ኃውስ ሮዝ ጋርደን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለአመታት ሲበዘብዙን የነበሩ አገራት ላይ ቀረጥ በመጣል የኢኮኖሚ ነጻነታችንን...
ከፌደራል መንግስት በኮቪድ ምክንያት ለስቴት ትምህርት ቤቶች የተሰጠውንና እስካሁን ወጪ ያልተደረገ ገንዘብ ወደካዝና ይመለሳል ተባለ። ማርች 28 በፌደራል የትምህርት...
ፕሬዘደንት ትራምፕ ከተለያዩ የአለም አገራት በሚገቡ የመኪና ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ መጣላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ይህ ታሪፍ ከኤፕሪል 2 ጀምሮ ተግባራዊ...
የ ዘ አትላንቲክ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጄፍሪ ጎልድበርግ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የጦር ኃይሎች የየመን ሁውቲዎችን ከመደብደባቸው 2 ሰዓት ቀደም...