ቨርጂንያ

በቨርጂንያ ግዛት ውስጥ የተከናወኑ ጉዳዮች እና የቨርጂንያ ግዛት ነዋሪዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ይመለከታል።

በቨርጂኒያ ግዛት ፍሬድሪክስበርግ የሊ ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሥስተኛ ክፍል ተማሪ መማሪያ ክፍል ውስጥ መሳሪያ ማምጣቱን ተክትሎ፤ ወላጆቹ በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸው የስፖትስልቫኒያ የፖሊስ ጽህፈት ቤት ገልጿል። ታዳጊው የጠዋት ስናክ ለመብላት እጁን ቦርሳ ውስጥ ከቶ በሚፈልግበት ሰዓት መሳሪያው መባረቁን ፖሊስ አስታውቋል። የፖሊስ ሃላፊ ሜጀር ኤሊዛቤት ስካት “መሳሪያ ታጣቂዎች እንዲህ ዓይነት ክስተት እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው” በማለት አሳስበዋል።  ፖሊስ ሰኞ ዕለት ከጠዋቱ 11 ሰዓት በፊት በተፈጠረው ክስተት ማንም አለመጎዳቱን ገልጾ፤ ስፍራውን እየተጠበቀ ተማሪዎች ክፍሉን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።  የታዳጊው ሁለቱም ወላጆቹ የአምስት ሺህ ዶላር ቦንድ እንዲከፍሉና የፊታችን አርብ በስፖትስላቬኒያ ካውንቲ የታዳጊዎች እና የቤት ውስጥ ጉዳይ ፍ/ቤት እንዲገኙ ታዘዋል።  የተማሪው መምህር ማንነታቸው ባይገለጽም በፍጥነት ተማሪዎቹን በማሰባሰብ እና ደህንነታቸውን በመጠበቅ ለወሰዱት እርምጃ ሙገሳ ተችሯቸዋል።  ፖሊስ አስፈላጊው የምክር እና የማረጋጋት አገልግሎት ለሊ ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መምህራን እና ወላጆች እየተሰጠ መሆኑም ገልጿል
የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ዛሬ ረቡዕ ኤፕሪል 9 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ የአሜሪካ የስደተኞች ቢሮ (USCIS)...
ኢትዮጲክ- እንግዳችን ስለሆንሽ እናመሰግናለን።እስቲ በቅድሚያ እራስሽን ለአንባቢዎቻችን አጠር አድርገሽ አስተዋውቂልን። መቅደስ – አመሰግናለሁ። ስሜ መቅደስ ገ/ወልድ ሆንዱራ ይባላል። ያው...
የላውደን ካውንቲ ሸሪፍ ቢሮ በሰሜናዊ ቨርጂንያ የመጀመሪያው የሆነውን በማረሚያ ቤቱ ያሉ የኢሚግሬሽን እስር ተዕዛዝ የተላለፈባቸውን ስደተኞችን ለፌደራል ኢሚግሬሽን አሳልፎ...
አይስ (ICE) ወደ ኤልሳልቫዶር ዲፖርት ያደረገው የቬንዙዌላ ዜጋ ስደተኛ በስህተት እንደሆነና በአስተዳደራዊ ግድፈት ምክንያት ይህ ሊፈጠር እንደቻለ አስታውቆ ነበር።...
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች እንዲሁም እንደ የአሸባሪ ጥቃት የመሳሰሉ ሰው ሰራሽ ጉዳቶች በተለያዩ አካባቢዎች እና ጊዚያት ይከሰታሉ።...
“እጃችሁን አንሱ” (Hands Off!) በሚል መርህ ቃል በመላው ዩናይትድ ስቴትስና በሌሎችም አገራት የፕሬዘደንት ትራምፕ አስተዳደርን የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ ለኤፕሪል...
የአሌክሳንድርያ ከተማ ለኤፕሪል ወር 2025 ክፍት የሆኑና ለከተማው አቅምን ያገናዘቡ የተባሉ የኪራይ ቤቶችን ዝርዝር ዛሬ ኤፕሪል 3 2025 ላይ...
ፕሬዘደንት ትራምፕ ዛሬ በዋይት ኃውስ ሮዝ ጋርደን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለአመታት ሲበዘብዙን የነበሩ አገራት ላይ ቀረጥ በመጣል የኢኮኖሚ ነጻነታችንን...

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.